G.M Mustefa Abasimel

G.M Mustefa Abasimel

የዋ/ስ/አ/ መልዕክት

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አሁን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትን የአዲስ አበባ- አዳማ እና የድሬደዋ- ደወሌ እንዲሁም በቀጣይ ግንባታቸው የሚጠናቀቁ የክፍያ መንገዶችን የማስተዳደር፣ የመጠገን፣ የክፍያ መንገድ አገልግሎት የመስጠት እና ተጓዳኝ ስራዎችን የመስራት ኃላፊነት ተሰጥቶት፤ በብቃት እየተወጣ ያለ ተቋም ነው፡፡

አገልግሎት ሰጪ ተቋም የሆነው ኢንተርፕራይዙ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለአፍታም ያልተቋረጠ የ24/7 አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ አገልግሎቱን ያለማቋረጥ የሚሰጠው ይህ ተቋም ቀልጣፋና ዘመናዊ በሆነ መልኩ የተጠቃሚዎቹን ፍላጎት ሲያሟላ ቆይቷል፡፡

ኢንተርፕራይዙ ምቹ፣ ዘመናዊ እና ፈጣን አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ የ24/7 የመንገድ ቁጥጥር ማድረጉ፤ ሰፊ የግንዛቤ መፍጠሪያ መርሃ ግብሮችን መጠቀሙ፤ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱ እንዲሁም የቅድመ አደጋ መከላከል፣ አደጋ ሲያጋጥም የመቆጣጠር እና በድህረ አደጋ ወቅት ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ አደጋን የማስተዳደር ተግባር ማከናወኑ ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ለመፍጠር አስችሎታል፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የአዲስ አበባ- አዳማ የፍጥነት መንገድ የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በለውጥ ሰራዊት አደረጃጀት የለውጥ መሣሪያዎችን በመጠቀም፤ ያለውን የሰው ኃይል በዕውቀትና በክህሎት በማሳደግ፤ የአሰራር ስልቶችን በማሻሻል በስፋት እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

ኢንተርፕራይዙ የቀጣይ አስር ዓመታት ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ለመግባት ዝግጅቱን አጠናቆ የጨረሰ ሲሆን፤ በሀገራችን የተስተዋለውን ለውጥ ከማስቀጠል አኳያ እና የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል መልካም አጋጣሚ ይፈጥርለታል፡፡ የተስተዋሉ ጥንካሬዎችንና ውጤቶችን ማስፋት፤ ስህተቶችን በማረም ለዛሬውና ለቀጣይ ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት በዘላቂነት ማሟላት ይገባል፡፡

የፋይናንስ አቅምን ማጎልበት፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን እና ቅልጥፍና ማሳደግ፤ ደህንነቱ የተጠበቀ የክፍያ መንገድ ማረጋገጥ፤ ደረጃውን የጠበቀ መንገድ እንዲኖር ማስቻል እንዲሁም የማስፈጸምና የመፈጸም አቅም በመገንባት የተቋሙን ውጤታማነት ማሳደግ የዕቅዱ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡

የክፍያ መንገዶች ጊዜን መቆጠባቸው፤ ደህንነትን መጠበቃቸው፤ የነዳጅ ወጪ መቀነሳቸው እንዲሁም ለተጨማሪ የጥገና ወጪ አለመዳረጋቸው በብዙ ደንበኞች ዘንድ ተመራጭ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡

በከተሞች መካከል ያለ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከራቸው፤ ለገቢ ወጪ ንግድ የትራፊክ እንቅስቃሴ ማሳለጫነት ጉልህ ሚና ያላቸው መሆኑ፤ በርካታ ወጣቶችን የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረጋቸው እንዲሁም ከአገልግሎት አሰጣጥ የሚገኘው ገቢ መንግስት በቀጣይ ተጨማሪ የክፍያ መንገዶች በመገንባት ላይ እንዲያተኩር ያደርጉታል፡፡

ኢንተርፕራይዙ ስድስት ዉጤታማ ዓመታት ያሰለፈ ሲሆን ከውጤታማነቱ ጀርባ ከምስረታው ጀምሮ ቦርዱን በሰብሳቢነት የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና በአሁኑ ወቅት የሚመሩት ኮ/ር ጄኔራል መላኩ ፈንታ ጠንካራ አመራር እና ውሳኔ ሰጪነት እንዲሁም የትራንስፖርት ሚ/ር ሲያደርግ የነበረው ከፍተኛ ድጋፍ እና ክትትል፤ የተቋሙ አመራሮች ያላሰለሰ ትጋት እና ከሁሉም በላይ ትጉህ እና የአገልጋይነት ባህሪን በተላበሱ ሥራ ወዳድ ወጣት ሠራተኞቹ ያበረከቱት አስተዋጽዖ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አሁን አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙትን እንዲሁም በቀጣይ ግንባታቸው ተጠናቆ የሚረከባቸውን የክፍያ መንገዶች ለማስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ አቅሙን ለማሳደግ ባለፉ ዓመታት የተገኙ ተሞክሮዎችን በመቀመር፤ የታዩ ውስንነቶችን በጥልቀት በመገምገም እና የማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰድ፤ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማዳበር ሃገራዊ ተልዕኮውን ለመፈጸም ይተጋል፡፡

G/M/ Message

The Ethiopian Toll Roads Enterprise is responsible for managing, maintaining, providing toll road services and related activities in the Addis Ababa-Adama, Dredewa-Dewele and Modjo- Batu toll roads that are currently in service and will be completed in the future. It is an efficient institution.

The enterprise, which is a service provider, has been providing uninterrupted 24/7 services since its inception. This institution, which continuously provides its services, has been meeting the needs of its users in an efficient and modern manner.

In addition to providing comfortable, modern and fast service, the enterprise also provides 24/7 road monitoring; Using broad awareness programs; Working in coordination with stakeholders As well as carrying out pre-disaster prevention and control in the event of an accident and risk management to prevent further damage during the post-disaster period. It allows that to create a safe environment.

The Addis Ababa-Adama Expressway, which is being serviced using modern technologies, is using tools of change in the organization of the Change Army to achieve superior performance; by increasing the existing workforce with knowledge and skills; It is being widely implemented by improving operational strategies.

Having completed the preparation for implementation by preparing a plan for the next ten years; It will create a good opportunity for us to continue the changes that have been observed in our country and to continue the journey of prosperity that we have started in a strengthened manner. Expanding on perceived strengths and outcomes; By correcting mistakes, it is necessary to sustainably meet the needs and interests of today and future generations.

Financial empowerment; Improving the quality and efficiency of service delivery; ensuring a secure payment method; Enabling a standardized way and increasing the effectiveness of the institution by building the capacity to implement and execute are the focus areas of the plan.

Toll roads save time; Keeping them safe; Lower fuel costs and less maintenance cost make them preferred by many customers.

Strengthening people-to-people relations between cities; The fact that they have a significant role in the traffic flow of income and expenditure business; The fact that many young people benefit from job opportunities and the income from service delivery makes the government focus on building more toll roads in the future.

The enterprise has had seven successful years, and behind its effectiveness is the strong leadership and decision-making of Prime Minister Dr. Abiy Ahmed, who has chaired the board since its inception, Commissioner Demelash G/Michael and the current leader, Colonel General Melaku Fenta, as well as the strong support provided by the Minister of Transport, and monitoring; It is the contribution of the management of the institution that is tireless and most of all the hard work and service minded young workers.

The Ethiopian Toll Roads Enterprise is currently providing services and will be able to manage the toll roads that will be completed in the future and to increase its service delivery capacity by summing up the experiences gained in the past years. By thoroughly evaluating identified limitations and taking corrective actions; It strives to fulfill its national mission by developing existing strengths.