የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ የሁለት ቀናት ስልጠናዊ ግምገማ አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ የሁለት ቀናት ስልጠናዊ ግምገማ አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕ ራይዝ

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ የሁለት ቀናት ስልጠናዊ ግምገማ አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ ከሐምሌ 16-17/2010 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ገልማ አባ ገዳ የስብሰባ ማዕከል ስልጠናዊ ግምገማ አካሂዷል፡፡ በግምገማውም የኢንተርፕራይዙ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተካፍለዋል፡፡

በውይይቱም በበጀት ዓመቱ የነበሩ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት ግምገማ የተደረገ ሲሆን የ2010 ዓ.ም የስራ አፈጻጸምን በጥልቀት መገምገም ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ከመድረኩ በመስጠት፤ የቀረቡ አስተያየቶች ላይ ውይይት በማድረግ እንዲሁም በ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ኢንተርፕራይዙ በ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ 10 ስትራቴጂካዊ ግቦች እንዲሁም 11 የማስፈጸሚያ ፕሮግራሞችን ነድፎ ሲተገብር ቆይቷል፡፡

በበጀት ዓመቱም 7,810,351 የትራፊክ ፍሰት በማስተናገድ ከክፍያ መንገድ አገልግሎት ብር 231,004,932 (ሁለት መቶ ሰላሳ አንድ ሚሊየን አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሁለት) መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን አፈጻጸሙም በ101.75% ሆኗል፡፡ በተጨማሪም ከልዩ ልዩ ገቢዎች ብር 13,885,685 (አስራ ሶስት ሚሊየን ስምንት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ አምስት) በማከል በአጠቃላይ ብር 244,890,617 (ሁለት መቶ አርባ አራት ሚሊየን ስምንት መቶ ዘጠና ሺህ ስድስት መቶ አስራ ሰባት) ገቢ በመሰብሰብ ከፍተኛ አፈጻጸም ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

ገቢን ከማሳደግ ባሻገር የመንገዱን ደህንነትና ምቾት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የክፍያ መሰብሰቢያ እና የክብደት ቁጥጥር ስርዓት ላይ ማሻሻያ በማድረግ እንዲሁም ወቅታዊ የመረጃ መጠባበቂያ ቋት በማሳደግ አገልግሎት መስጠቱ፤ ለበርካታ የአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል በመፍጠር እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ  በመሳተፍ ከማህበረሰቡ ጎን መቆሙን ማሳየቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖች ሆነው ተጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው ኢንተርፕራይዝ አለም አቀፍ የፋይናንስ መረጃ አያያዝና አመዘጋገብ ስርዓት (IFRS) ትግበራ መዘርጋት፤ የችግኝ ማፍያ ጣቢያ ማልማት ፕሮጀክቶች ተጠቃሽና አበረታች ስራዎች ሆነው ተነስተዋል ፡፡

ከተሳታፊዎችም በቀጣይ የክፍያ መንገዱን በራስ አቅም ለመጠገን ያለ ዝግጁነት ምን ይመስላል? ኢንተርፕራይዙ እየተገነቡ ያሉ የክፍያ መንገዶችን ተረክቦ ለማስተዳደር የተገኙ ተሞክሮዎች እንዴት ይታያሉ? የሚሉና በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከመድረኩም ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ ከክፍያ መንገድ አገልግሎት 8,869,916 የተሽከርካሪዎች ምልልስ በማስተናገድ ብር 265,728,641.57 (ሁለት መቶ ስልሳ አምስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሀያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አንድ) ለመሰብሰብ ዕቅድ ተይዟል። በመንገዱ ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን 40% ለመቀነስ በርካታ ስራዎች እንደሚሰሩ ተጠቅሷል፡፡

 

በቀጣይም የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ከዚህ በተሻለ መልኩ በማስቀጠል እንዲሁም የተስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም የኢንተርፕራይዙን ራዕይ ከግብ ማድረስ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥና የጋራ አቋም በመያዝ ስልጠናዊ ግምገማው ተጠናቋል፡፡

 

ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!