ተቋማዊ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ትግበራ!

ተቋማዊ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ትግበራ!

ተቋማዊ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ትግበራ!

ኢትዮጵያ በመንገድ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ እምርታ እያሳየች ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የዓለምን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ተከትሎ የፍጥነት መንገዶች በስፋት መዘርጋታቸው ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት የሚኖረው ፈይዳ ከፍተኛ ነው፡፡ ዘርፉ ከቦታ ቦታ ያለን እንቅስቃሴ በማፋጠን፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር፣ ወጪና ገቢ ንግድን በማቀላጠፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በሀገሪቱ የሚገነቡ የክፍያ መንገዶችን ለማስተዳደር እንደ መቋቋሙ የአዲስ በባአዳማ የክፍያ መንገድን እያስተዳደረ ይገኛል፡፡ በዚህም የክፍያ መንገዱን ከመጠገን ጀምሮ ያሉ ተጓዳኝ ስራዎችን  መስራት፤ በቀጣይም የሚገነቡ የክፍያ መንገዶችን ተረክቦ ለማስተዳደር ልምዶችን በማጎልበት የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት እየተወጣ ያለ ተቋም ነው፡፡

ኢንተርፕራይዙ የራሱን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ በመግባት ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው፡፡ የስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዋና አላማ ኢንተርፕራይዙ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውን አዋጅ መሰረት ማድረግ የተጣለበትን ተልዕኮ መወጣት፤ ከመንገድ ልማት ዘርፍ ፈጣን ዕድገት ጋር የሚጣጣም ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት እንዲሁም የጨመረ ገቢና ተልዕኮን ማሳካት የቻለ የሰው ሃብት ማፍራት ነው፡፡ የስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ፋይናንስ፣ ተገልጋይ፣ የውስጥ አሰራር እንዲሁም መማርና ዕድገት ናቸው፡፡ ከዚህ በመነሳት የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡

ዓላማውን ከግብ ማድረስ የሚችል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ለማየት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማለትም ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ ሠራተኞች፣ አጋር ተቋማት፣ ደንበኞች እንዲሁም በቀጥታም ይኹን በተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸው ሁሉ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡