የተሽከርካሪ ፍሰት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር 6.35% ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የተሽከርካሪ ፍሰት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር 6.35% ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የተሽከርካሪ ፍሰት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር 6.35% ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የሚያስተዳድረው የአዲስ- አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ በ2011 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ፍሰት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር 6.35% ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በቀን በአማካይ ከ 21 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን እያስተናገደ የሚገኘው የፍጥነት መንገድ ያልተቋረጠ የ24/7 የክፍያ መንገድ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህም በ2011 ዓ.ም ሦስት ወር 2,071,381 ተሽከርካሪዎችን በማስተናገድ ብር 61,346,105 (ስድሳ አንድ ሚሊየን ሦስት መቶ አርባ ስድስት ሺህ አንድ መቶ አምስት) መሰብሰብ ችሏል፡፡

ይህ ገቢ ቀጥታ ከክፍያ መንገድ አገልግሎት የተገኘ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ከልዩ ልዩ ገቢ ማለትም ከማስታወቂያ ቦታ ኪራይ፣ ከመንገድ ሀብት ጉዳት ካሳ ክፍያ፣ ከክሬን… አገልግሎቶች 2,806,523 (ሁለት ሚሊየን ስምንት መቶ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ሦስት) ተሰብስቧል፡፡

በአጠቃላይ ከተለያዩ አገልግሎቶች ብር 64,152,628.00 (ስድሳ አራት ሚሊየን መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ስምንት) በላይ ማስገኘት የቻለው የአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ በቀጣይም የአገልግሎት ደህንነትንና ጥራትን በጠበቀ መልኩ የደንበኞችን ፍላጎት በማርካት ገቢውን ለማሳደግ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡