የድሬዳዋ ደወሌ የክፍያ መንገድ አገልግሎትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

የድሬዳዋ ደወሌ የክፍያ መንገድ አገልግሎትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

የድሬዳዋ ደወሌ የክፍያ መንገድ አገልግሎትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

 

በቅርቡ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት የሚገባው የድሬዳዋ ደወሌ የክፍያ መንገድ ስራ ለማስጀመር እንዲያግዝ ስራው ሲጀምር አጋዥ ከሆኑ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በድሬዳዋ ከተማ ውይየት ተካሂዷል፡፡

 

የድሬደዋ ደወሌ መንገድ ርዝመት 220 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን ከዚህ ቀደም አንድ ቀን ይፈጅ የነበረውን ጉዞ ወደ ግማሽ ቀን ይቀንሳል፡፡ የክፍያ መንገዱ ከ2 ወራት በኋላ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆንም ተገልፆዋል፡፡ ይህን የክፍያ መንገድ የሚያስተዳድረው የ

ኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ሲሆን ስራውን ለመጀመር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ካከናውናቸው ስራዎች መካከል ለአገልግሎቱ ቅልጥፍና የሚያግዙ አቅርቦቶችን ከሚሰጡ ተቋማት ጋር ትስስር መፍጠር ከድሬዳዋና ከሶማሌ ክልል ሺንሌ ዞን አስተዳደር ኃላፊዎች፤የፀጥታ አካላት፤ በመንገዱ መስመር ከሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፤ከሃይማኖት አባቶች ፤ኡጋዝ እና አባ ገዳዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም ለስራው ግብዓት የሚሆን ሃሳቦች ተገኝተዋል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊወች ለክልሉ የሚያስገኘውን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ፋይዳ ታሳቢ በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ  እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡