የማስታወቂያ ቦታ ኪራይ…

የማስታወቂያ ቦታ ኪራይ…

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ-አዳማ የፍጥነት መንገድን በማስተዳደር ላይ ይገኛል ፡፡ የፍጥነት መንገዱ በሀገራችን የመጀመሪያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዘርፉን በማስተዳደር ረገድ አዲስ ልምድ እየተገኘበት ነው ፡፡ የፍጥነት መንገዱ አብዛኛው የሀገራችን ወጪ እና ገቢ ንግድ የሚተላለፍበት መስመር መሆኑ፤በከተሞች መካከል የሚኖር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከሩ፤ ለበርካታ የአካባቢው ህብረተሰብ የስራ ዕድል መፍጠሩ የሚጠቀሱ ፋይዳዎች ናቸው፡፡ ኢንተርፕራይዙ በአሁኑ ወቅት በዋናነት እየሰጠ ካለው የክፍያ መንገድ አገልግሎት በተጨማሪ በርካታ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ እያቀረበ ነው፡፡

ከእነዚህም ውስጥ የማስታወቂያ ቦታ ኪራይ ተጠቃሽ ነው፡፡ ገቢ ሊያስገኝ የሚያስችል የማስታወቂያ ቦታ ኪራይ ስራ የማስታወቂያ ቦታ ኪራይ… ዘርፍ በስፋት በመንገዱ ላይ በሚገኙ የመሸጋገሪያ ድልድዮች ላይ ምርትና አገልግሎታቸውን ማስተዋወቅ ለሚፈልጉ ድርጅቶች የማስታወቂያ ቦታ ኪራይ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ፡፡ የማስታወቂያ ቦታ ኪራይ አንድ የገቢ ምንጭ ከመሆኑም በተጨማሪ በመንገዱ ውበት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ በማድረግ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከፍ ያደርጋል፡፡ እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበትን አጋጣሚ ይፈጥራል፡፡ የክፍያ መንገዱ በቀን ከሃያ አንድ ሺ በዓመት ደግሞ ከሰባት ነጥብ ስምንት ሚሊየን በላይ ተሽከርካሪዎች ማስተናገዱና ለሃያ አራት ሰዓት ያልተቋረጠ አገልግሎት መስጠቱ እንዲሁም በበርካታ ተመልካቾች እይታ ውስጥ መዋሉ በማስታወቂያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ ሁልጊዜም ያልተቋረጠ የ24/7 አገልግሎት የሚሰጠው የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በቀጣይም አገልግሎቱን በማስፋትና ተደራሽ በማድረግ እርካታው ከፍ ያለ ተገልጋይ ለማየት ተግቶ ይሰራል፡፡