የመንገድ ደህንነት እና የአካባቢ ፀጥታ ጉዳይ…

የመንገድ ደህንነት እና የአካባቢ ፀጥታ ጉዳይ…

የመንገድ ደህንነት እና የአካባቢ ፀጥታ ጉዳይ…

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ መጋቢት 14/2011 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ትኩረቱን የመንገድ ደህንነት እና የአካባቢ ፀጥታ ጉዳይ ላይ ያደረገ ውይይት አካሄዷል፡፡

በዕለቱም ጥሪ የተደረገላቸው የከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች፣ የፖሊስ ኮሚሽነሮች፣  የትራፊክ ፖሊስ ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የአካባቢ ማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በውይይቱ መነሻ ሃሳብ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሃሳብ ላይ ቤቱ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡ ወቅታዊ የጉዞ ደህንነት ስጋቶች ስለማስቀረት፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቀጣይነት ባለው መልኩ ተቀናጅቶ ስለመስራት፤ ማህበራዊ ኃላፊነትን ስለመወጣት፤ የሌሎች ሃገራት ተሞክሮዎችን ስለመቀመር እንዲሁም የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮችን ስለማመቻቸት የተነሱ ሃሳቦች ነበሩ፡፡

የኢንተርፕራይዙ ኃላፊዎች ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የተሰጡ አስተያየቶች ገንቢ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ስለሆነም ከመቼውም በላይ በመንገድ ደህንነት እና የአካባቢ ፀጥታ ጉዳይ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ እንዲሁም ማህበራዊ ኃላፊነቶችን ለመወጣት በርካታ ጥረቶች ቢደረግም በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡

የኢንተርፕራይዙ ዋ/ስ/አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ ከድር የምክክር መድረኩ መዘጋጀት ጠቃሚ በመሆኑ በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመግለፅ ሁሉም አካላት ከኢንተርፕራይዙ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ በማሳሰብ ውይይቱን አጠቃለዋል፡፡