የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2011 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2011 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2011 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በተያዘው የበጀት ዓመት እቅድ አስራ አንድ ስትራቴጂካዊ ግቦች እንዲሁም ዘጠኝ የማስፈጸሚያ ፕሮግራሞችን ነድፎ ሲተገብር ቆይቷል፡፡

በዘጠኝ ወራትም 6,382,800 የትራፊክ ፍሰት በማስተናገድ ከክፍያ መንገድ አገልግሎት ብር 191,470,903 (አንድ መቶ ዘጠና አንድ ሚሊየን አራት መቶ ሰባ ሺ ዘጠኝ መቶ ሶስት) ተሰብስቧል፡፡ በተጨማሪም ከልዩ ልዩ ገቢዎች (ከማስታወቂያ ቦታዎች ኪራይ፣ ከተሽከርካሪ ማንሻና መጎተቻ…) ብር 13,326,299 (አስራ ሦስት ሚሊየን ሦስት መቶ ሃያ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ዘጠኝ) በመሰብሰብ በአጠቃላይ ብር 204,797,202 (ሁለት መቶ አራት ሚሊየን ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሁለት) መሰብሰብ ተችሏል፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አገልግሎት አየሰጠ የሚገኘው የአዲስ አበባ -አዳማ የፍጥነት መንገድ የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በለውጥ ሰራዊት አደረጃጀት የለውጥ መሣሪያዎችን በመጠቀም፤ የተፈጠሩ መልካም አጋጣሚዎችን በመንቀስ፤ ያሉትን ጠንካራ ጎኖች አጠናክሮ በማስቀጠል፤ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም፤ የሚስተዋሉ ድክመቶችን በመቅረፍ፤ ያለውን የሰው ኃይል በዕውቀትና በክህሎት በማሳደግ፤ የአሰራር ስልቶችን በማሻሻል በስፋት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡

አገልግሎቱን በስፋት እያስኬደ የሚገኘው የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በያዝነው ዓመት ዘመናዊ የክፍያ አሰባሰብ ስርዓት በመጠቀም ለክፍያ መንገድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

የመንገዱን ደህንነት ከማስጠበቅ አኳያ የተለያዩ የግንዛቤ መፍጠሪያ መርሃ ግብሮችን በማዘጋጀት እና በመንገዱ ክልል ውስጥ የ24 ሰዓት የመንገድ ላይ ቅኝታዊ ቁጥጥር በማድረግ እንዲሁም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ተሰርቷል፡፡ በተጨማሪም የጥገና አቅምን በማሳደግ በአገልግሎት እድሜ ማብቃት እና በአደጋ ምክንያት በንብረቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን በአፋጣኝ በመጠገን የመንገዱ ምቾት እንዳይጓደል እየሰራ ነው፡፡

የአገልግሎት አሰጣጡን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ የሚገኘው የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን የመንገድ ላይ መብራት ማስፋፊያ ዝርጋታ፣ የአገልግሎት መስጫ ጣቢያና የደንበኞች የጥሪ ማዕከል ግንባታ፣ የክፍያ አሰባሰብ ስርዓት ማሻሻያ እንዲሁም የስራ ቦታን ምቹ (Ergonomics) ከማድረግ አንጻር የማሻሻያ ፕሮጀክቶች የሚጠቀሱ ስራዎች ናቸው፡፡

ግምገማውን ትኩረት ያደረገው ተቌሙ የተያዙ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸዉ የጊዜ ገደብ ማስኬድ አለመቻሉ እንዲሁም በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሱ የሞት ቁጥርን በተፈለገዉ መጠን መቀነስ አለመቻሉ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን ነው፡፡

አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አራት ዓመት ተኩል በላይ ያስቆጠረው የአዲስ አበባ -አዳማ      የፍጥነት መንገድ ያልተቌረጠ የ24/7 የክፍያ መንገድ አገልግሎት መስጠቱ፤ በኢንተርፕራይዙ የመንገድ አካፋይ ላይ የሚገኙ ንብረቶች በወቅቱ መጠገኑ፤ የድሬዳዋ – ደወሌ የክፍያ መንገድ ስራ ለማስጀመር ዝግጅቶችን ማጠናቀቁ፤ ውጤታማና ዘመናዊ የሆነ የአረንጓዴ ልማት አሰራርን መተግበሩ የተነሱ ጠንካራ ጎኖች ሆነው ተነስተዋል፡፡ በዘጠኝ ወራትም የውጤት ተኮር ስርዓት ዕቅድ አፈፃፀም አጠቃላይ ውጤት 86.5% ሲሆን የአፈፃፀም ደረጃውም ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በቀጣይም በዘጠኝ ወራት የታዩ ደካማ ጎኖችን በጥልቀት በመመርመርና ማስተካከያ በማድረግ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማዳበር ከዚህ በተሻለ መልኩ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ የኢንተፕራይዙን ራዕይ ከግብ ማድረስ እንደሚገባ አቅጣጫ  በመስጠት ግምገማው ተጠናቌል፡፡

ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!