ጥገና

ጥገና

ጥገና

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የሚያስተዳድረው የአዲስ አበባ- አዳማ የክፍያ መንገድ ደህንነቱ ተጠብቆ እና ምቾቱ ተረጋግጦ መቀጠል እንዲችል በርካታ የጥገና ስራዎች ሲከውኑ ቆይቷል፡፡

በመንገዱ ላይ የሚገኙ የግጭት መከላከያ ብረቶችን (guardrail)መጠገን ተችሏል በዚህም በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ብረቶች 5.88 ኪ.ሜ የሚሸፍን ጥገና አካሄዷል፡፡

1041 አንፀባራቂዎች እና 1333 አረንጓዴ የብርሃን መከላከያዎች (greensheld) ተጠግኗል፡፡

የመንገዱ አጥር ጉዳት ሲደርስበት በመንገዱ ላይ የደህንነት ስጋቶች ለማስቀረት 3.44 ኪ.ሜ የሚሸፍን የአጥር ጥገና ማከናወን ተችሏል፡፡

በቀጣይ በአገልግሎት ጊዜ ማብቃት ምክንያት ወይም በግጭት እና ጉዳት ደርሶባቸው አገልግሎት መስጠት የሚያቆሙትን የመንገድ ሃብቶች በብቃት በመጠገን፤ ተልዕኮን መወጣት እንዲያስችል፤ አነስተኛ እና መለስተኛ ጥገናዎች በውስጥ አቅም ለመከወን እንዲሁም ከፍተኛ ጥገናዎችን ለመተግበር የሚያስችል የጥገና አቅም በመፍጠር፤ ብቃት ያለው የሰው ኃይል በማፍራት እና ዘመናዊ መሳሪያ በማቅረብ የተደራጀ የጥገና መዋቅር ማረጋገጥ ይገባል፡፡