የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ኢንተርፕራይዙ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡

የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ኢንተርፕራይዙ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በአዋጅ ከተሰጠው መንገዱን የማስተዳደርና የማስጠገን ተልዕኮ ባሻገር ከቅድመ እስከ ድህረ አደጋ ድረስ ያለውን የቁጥጥር ስራ በማጠናከር የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በሀገራችን በየትኛውም አካባቢ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋ መንስኤዎች በርካታ ቢሆኑም ከአሽከርካሪው መልካም ያልሆነ የማሽከርከር ባህሪ አንፃር ፤ የትራፊክ ህጎችን አለማክበር እና የተሸከርካሪው የቴክኒክ ሁኔታ ለአብዛኛው የትራፊክ አደጋ እንደዋነኛ ምክንያት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ችግሮችም በተመሳሳይ በአዲስ አዳማየ ፍጥነት መንገድ እንዲሁም በድሬደዋ ደወሌ የክፍያ መንገዶች ላይም ይስተዋላሉ፡፡

በመሆኑም እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ከመንገዶቹ መግቢያና መውጭያ ባሻገር በመንገዱ አቅራቢያ በሚገኙ ከተሞች መናሃሪያዎች ውስጥ እንዲሁም መንገዱን በአብዛኛው የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎች ሚነሱባቸው ከተሞች ላይ በመገኘት በርካታ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በዚህም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር አደጋውን በ 50% ፐርሰንት መቀነስ ተችሏል፡፡ ይህን ስራም በቀጣይ በተመረጡ ቦታዎች ተጠናክሮ እንደሚሰራም የኢንተርፕራይዙ የትራፊክ ደህንነትና የመንገድ ቁጥጥር ቡድን አስታውቋል፡፡