ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ ለማድረግ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተገለፀ፡፡

ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ ለማድረግ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በአዲስ- አዳማ የፍጥነት መንገድ ዙሪያ ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ አደአ ወረዳ 1390 ለሚሆኑ የደንካካ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከ514,653 (አምስት መቶ አስራ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ሶሰት) ብር በላይ ወጪ በማድረግ ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል፡፡

የመጠጥ ውሃ ግንባታው ተጠናቆ ርክክብ በተደረገበት ወቅት በስፍራው የተገኙ ነዋሪዎች ኢንተርፕራይዙ የማህበረሰቡን ችግር ተረድቶ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን በማቅረብ ከዚህ በፊት ንፁህ ውሃ ለማግኘት የሚያደርጉትን እንግልት ከማስቀረት አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገላቸው ጠቁመዋል፡፡

ኢንተፕራይዙን በመወከል በስፍራው የተገኙት የተቋሙ የሰው ሀብት ልማት እና ፋሲሊቲ መምሪያ ኃላፊ ኮ/ል ጳውሎስ ከበደ እንደተናገሩት ላለፉት አምስት አመታት ኢንተፕራይዙ የተሰጠውን ተልዕኮ ከመፈፀም ባሻገር በአካባቢው የሚስተዋሉ ማህበራዊ ችግሮችን ከመቅረፍ ረገድ በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን አስታውሰው ህብረተሰቡም ከኢንተርፕራይዙ ጎን በመሆን የመንገዱን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡና ከኢንተርፕራይዙ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡