Version | |
Download | 14 |
Stock | ∞ |
File Size | 27.82 KB |
Create Date | December 10, 2017 |
Download |
የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 310/2014 መሰረት የሚከተሉትን ዋና ዋና ዓላማዎች ለመፈጸም የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡
- ለመንገድ ተጠቃሚዎች የክፍያ መንገዶች አገልግሎት መስጠት፣
- የክፍያ መንገዶችን የማስተዳደርና ማስጠገን፣
- በክፍያ መንገዶች ክልል ውስጥ የተሰሩ የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን የማስተዳደር፣ እና
- ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ሥራዎችን ማካሄድ፣
1.2.1 ተልዕኮ
ዘመናዊ በሆነ ቴክኖሎጂና ብቃት ባለው የሰው ሀብት በመጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ፣ምቹ፣ዘመናዊ፣ፈጣንና አስተማማኝ የክፍያ መንገድ አገልግሎት መስጠት፣ማስተዳደርና መጠገን፡፡
1.2.2 ራዕይ
በ2017 በመንገድ ደህንነትና በአገልግሎት ጥራት በአፍሪካ ቀዳሚ የክፍያ መንገድ ሆኖ ማየት፡፡
1.2.3 እሴቶች
- ደህንነት
- ተገልጋይተኮር
- ተጠያቂነት
- ጥራት
- የቡድንስራ
- ለአካባቢተቆርቋሪነት
- ዘመናዊነት
- አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የፍጥነት መንገድ ደህንነት አሰራር መዘርጋት፤
- የማይቋረጥ የ24/7 የክፍያ መንገድ አገልግሎት መስጠትና ክፍያ መሰብሰብ፤
- የፍጥነት መንገዶች አካላት ጥገናና የዕድሳት ስራ ማከናወን፤
- በፍጥነት መንገድ ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን ክብደት መቆጣጠር፤
የአካባቢ ጥበቃ ስራ ማከናወን
- በተቋሙ የሚሰጡትን አገልግሎቶች የመጠየቅና በቻርተሩ በተቀመጡ ስታንዳርዶች መሰረት አገልግሎት የማግኘት፤
- አስፈላጊና የተሟላ መረጃ የማግኘት፤
- በፍጥነትና በቅልጥፍና የመስተናገድ፤
- ባገኙት አገልግሎት ላይ አስተያየት የመስጠት፤
- ቅሬታ ካላቸው በተቀመጠው ስርዓት መሰረት የማቅረብና ፈጣን ምላሽ የማግኘት፣
- ብልሹ አሰራሮችን እና ሙስናን የማጋለጥ፣
- የማያረካ እና በቂ ምላሽ ባጡበት ጊዜ ለሕዝብ እምባ ጠባቂ ለሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለሚዲያ እንዲሁም ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የማሳወቅ።
4
- ላስቀመጥናቸው እሴቶች እንገዛለን!
- ሁሌም ለደህንነትዎ ቅድሚያ እንሰጣለን!
- በቻርተሩ በተቀመጠው ደረጃ ለተገልጋዮቻችን አገልግሎት ለመስጠት በፍፁም ተባባሪነት፣ ተዓማኒነትና ተጠያቂነት ተግተን እንሰራለን!
- ለሰጠናቸው አገልግሎቶችና ለወሰንናቻው ውሳኔዎች ተጠያቂዎች ነን!
- ለተገልጋዮች ጥያቄዎች፣ አስተያየት እና ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን!
- ሁሌም ለጥራት እንተጋለን!
- በሠለጠነ፣በላቀ አሰራር እና አገልግሎት ተገልጋይን እናረካለን!
በክፍያ መንገዱ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች በአይነታቸውና በሚጓዙት ርቀት መሰረት የተለያየ መጠን ያለው የአገልግሎት ክፍያ የሚጠየቁ ሲሆን ዝርዝሩም ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ተገልጿል፡፡
የተሽከርካሪው ዓይነት | የክፍያመጠን በብር ከቱሉ ዲምቱ
እስከ |
||||
የክፍያው ቦታ/ጣብያ | ቢሾፍቱ ሰሜን | ቢሾፍቱ ደቡብ | ሞጆ | አዳማ ሀ እና ለ | አዳማ ዋና |
አነስተኛና መለስተኛ | 10 | 20 | 35 | 40 | 50 |
ሚኒባስ | 10 | 20 | 35 | 40 | 50 |
መካከለኛ ባስና ቀላል ክብደት ያላቸው | 10 | 20 | 35 | 40 | 50 |
ከፍተኛ መጠን ያላቸው ባስና መካከለኛ ጭነት | 10 | 25 | 40 | 45 | 60 |
ከፍተኛ ጭነት (ባለ 4 ጎማ ተሸካሚ) | 15 | 30 | 45 | 55 | 70 |
ከፍተኛ ጭነት(ባለ 5 ጎማ ተሸካሚ) | 15 | 30 | 45 | 55 | 70 |
ተሳቢ ጭነት (ባለ 6 ጎማ ተሸካሚና ከዚያ ላይ) | 15 | 30 | 45 | 55 | 70 |
*ሁሉም ክፍያ ቫትን/VAT/ጨምሮበብር የሚፈፀም ነው።
11
መደብ | የመኪና አይነት | የክፍያ መጠን |
1ኛ | የቤት መኪናና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 800 ብር |
2ኛ | ሚኒባስ፣ አይሱዙና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 1000 ብር |
3ኛ | የህዝብ ማመላለሻ፣ ሲኖትራክ፣ ኤፍ.ኤስ.አር.፣ ቅጥቅጥና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 1500 ብር |
4ኛ | ተሳቢና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 2000 ብር |
*ሁሉም ክፍያ ቫትን/VAT/ሳይጨምር በብር የሚፈፀም ነው።
መደብ | የመኪና አይነት | ክፍያ በአንድ ኪሎሜትር |
1ኛ | የቤት መኪናና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 80 ብር |
2ኛ | ሚኒባስ፣ አይሱዙና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 95 ብር |
3ኛ | የህዝብ ማመላለሻ፣ ሲኖትራክ፣ ኤፍ.ኤስ.አር.፣ ቅጥቅጥና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 115 ብር |
4ኛ | ተሳቢና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 140 ብር |
*ሁሉም ክፍያ ቫትን/VAT/ሳይጨምር በብር የሚፈፀም ነው።
መደብ | የመኪና አይነት | የክፍያ መጠን |
1ኛ | የቤት መኪናና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 200 ብር |
2ኛ | ሚኒባስ፣ አይሱዙና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 225 ብር |
3ኛ | የህዝብ ማመላለሻ፣ ሲኖትራክ፣ ኤፍ.ኤስ.አር.፣ ቅጥቅጥና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 250 ብር |
4ኛ | ተሳቢና የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች | 300 ብር |
*ሁሉም ክፍያ ቫትን/VAT/ሳይጨምር በብር የሚፈፀም ነው።