Transport Minister


Version
Download26
Stock
File Size256.81 KB
Create DateMay 23, 2017
Download

ኢትዮጵያ ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ረድፍ ውስጥ ለመግባት የትራንስፖርት መሠረተ‑ልማቷ እና አገልግሎቷ ማደግ እና ቀድሞ መገኘት ለሌሎች የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና አገልግሎት ዘርፎቿ ዕድገት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል። የተጠናከረ ፖለቲካዊ አስተዳደር ለመዘርጋት የምታደርገውን ጥረትንም በማገዝ አንድ የተጠናከረ የሶሻል፣ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ማኅበረሰብ በመፍጠር ረገድም ሚናው የጎላ ነው።

መንግስት ሀገሪቱ ትታወቅበት ከነበረው አስከፊ የድህነት ገጽታዋ በመሠረታዊነት ለመቀየር የሚያስችሉ የልማት ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ እና መላው ሕዝብ፣ የግሉ ዘርፍ እና ሌሎችም የልማት አጋሮች ለተግባራዊነቱ ባደረጉት የነቃ ተሳትፎ ሁለንተናዊ የልማት ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው። ፖሊሲዎቹን እና ስትራቴጂዎቹን ውጤታማ በማድረግ ረገድ በተለያየ የልማት ዕቅድ ዘመን ሲተገበሩ የቆዩ የልማት ዕቅዶች አስተዋጾ አድርገዋል። በመሆኑም ፈጣን እና ተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ  እና በዚህ ረገድ በተለይ ከ1995‑1997 ሲተገበር  የነበረው የዘላቂ ልማት እና የድህነት ቅነሳ ፕሮግራም፣ ከ1998‑2002 የተተገበረው ድህነትን ለማስወገድ ፈጣን እና ዘላቂ ልማት ዕቅድ (A Plan for Accelerated and Sustained Development to End Poverty-PASDEP) እንዲሁም የዕቅድ ዘመኑ እየተገባደደ የሚገኘው የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (2003‑2007) በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

የመጨረሻው የልማት ዕቅድ መላ ሕዝቡን በምልዓት በማሳተፍ፣ የግሉ ዘርፉንም በተነቃቃ ሁኔታ በማሳተፍ ብሎም የልማት አጋሮችን ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ትብብር በአስደናቂ ሁኔታ በመሳብ ሀገሪቱ ለተያያዘችው መዋቅራዊ ሽግግር መዳላድል በመፍጠር ረገድ ብዙ ርቀት እንዳስኬደ ይታመናል። የእስካሁኑ የልማት ዕቅዱ አፈጻጸምም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በልማት ዕቅዱም ትኩረት ከተሰጣቸው አብይ ዘርፎች ውስጥ አንዱ የትራንስፖርት ዘርፍ  ሲሆን፥ በዚህም ዘርፉ የኢኮኖሚውን ዕድገት በማስቀጠል ብሎም ይበልጥ ተኪ የሌለው የደጋፊነት ሚናውን በላቀ ሁኔታ እንዲወጣ የሚያስችሉ የተለያዩ ውጥኖችን በመያዝ ለተግባራዊነታቸው ርብርቦሽ ሲደረጉ ቆይተዋል። በተለያየ ደረጃ የሚገለጹ መልካም አፈጻጸሞችም ተመዝግበውባቸዋል።

በዕቅድ ዘመኑ የተመዘገቡ የዘርፉ የልማት ውጤቶችን ለማስቀጠል የሚያስችል ግን ደግሞ የትራንስፖርት ዘርፉ የወደፊቱ የዕድገት ዕይታን ባገናዘበ መልኩ የትራንስፖርት ዘርፍ የሁለተኛው አምስት ዓመት (2008-2012) የልማት ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ሥራ መግባት ይጠይቃል።