Information & Monitoring

Information & Monitoring

በዘመናችን ዓለም የደረሰችበት ደረጃ ሲታሰብ መንገዶች ከመነሻ መድረሻ የሚያሻግሩ ሆነው የሰው ልጆችን በፖለቲካ ፤ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ሕይወታቸውን የሚያተሳስሩ አይነተኛ መሳሪያ ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ በየዘመኑ የሚወጡ የምርምር ውጤቶች በዘመናዊ መንገድ ግንባታ ላይ አወንታዊ ተጽእኖ አሳርፈዋል፡፡ የሰው ልጆች በዚህ ቴክኖሎጂ ታግዘው  የእለት ከእለት ኑሮን ለማሸነፍ በሚደረገው እንቅስቃሴ ሕይወትን ቀላል ለማድረግ ችለዋል፡፡ በተለይም ዘመናዊነትን    በምድር፤ በባህር እና በአየር የሚደረገውን የጉዞ እንቅስቃሴ ከመቼውም በላይ ማዘመን ችለዋል፡፡  በዚህም  የሰው ልጆችን የእድገት ደረጃው በከፍተኛ ፍጥነት በማሳደግ ላይ ናቸው ለማለት ይቻላል፡፡

ለአገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የአዲስ አበባ አዳማ የክፍያ መንገድም በዓይነቱ ዘመናዊ የመንገድ አውታር አካል ነው ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

ይህንን መንገድ ዘመናዊ ነው ከሚያሰኙት ባህርያት አንዱ መንገዱ ሲሲ ቲቪ በሚባል ዘመናዊ የአይቲ ቴክኖሎጂ እየታገዘ የእለት ከእለት ተግባሩን በቀን ለ24 ሰዓታት የትራፊክ ፍሰቱ ሳይስተጓጎል፤ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህ መንገድ ላይ ዘመናዊ የመንገድ ላይ ካሜራ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የእያንዳንዱ ተሸከርካሪ ዓይነት፤ የሰሌዳ ቁጥራቸው፤ የተጠቀሙበት መግቢያና መውጫ በሮች፤ የተከፈለው የገንዘብ መጠን፤ እና ሌሎችንም ለይቶ መረጃን በየክስተቱ እያከማቸ የሚሰራበት  ዘመናዊ አስራር ነው፡፡

ከዚህ ሌላ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች መንገዱን የሚጠቀሙትን አካላት በነዚሁ ካሜራዎች በመጠቀምና ሲስተሙን አጠቃሎ በሚያሳይ አንድ ክፍል ውስጥ በመሆን፤ ሁለንተናዊ ሂደቱን በሚቆጣጠር በባለሙያ እየታገዙ ማረጋገጫ የሚሰጥበት ስፍራ ነው፡፡

በዚህ ስፍራ በመንገዱ ላይ የሚከሰት ማናቸውንም አደጋ፤ የትራፊክ እንቅስቃሴ፤ ሰራተኞች በስራ ላይ ስለመሆናቸው እና የሌሎች ግለሰቦችን እንቅስቃሴ መከታተያ ክፍል ነው፡፡ ከዚህ ሌላ በየእለቱ የተሽከርካሪ ፍሰትን  እና የተሰበሰበ ገንዘብ መጠን በቴክኖሎጂው በመታገዝ የምናገኝበት ማእከል ነው፡፡