በሃገሪቱ የታየውን ለውጥ ለማስቀጠል የሁሉም ሠራተኛ ሚና የጐላ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በሃገሪቱ የታየውን ለውጥ ለማስቀጠል የሁሉም ሠራተኛ ሚና የጐላ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በሃገሪቱ የታየውን ለውጥ ለማስቀጠል የሁሉም ሠራተኛ ሚና የጐላ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ሰራተኞች እና አመራሮች ህዳር 2012 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በቀጣይ አስር ዓመት የሚተገበር መሪዕቅድ ላይ እንዲሁም በሃገሪቱ ለውጥ የሠራተኛው ሚና በሚል ውይይት አካሄደዋል፡፡

በመድረኩ መንግስት አጠቃላይ ለውጡን አስመልክቶ በተለያዩ ዘርፎች አበረታች ውጤቶች ማስመዝገቡን በማንሳት የታዩ ጠንካራ ጐኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል፤ የተፈጠሩ መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም እና ለተስተወሉ ክፍተቶች ማስተካከያ በማድረግ ለውጡን ማስቀጠል እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡

ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ዓመታት የሚተገበረው ዕቅድ ለትራንስፖርት ዘርፉ የረዥም ጊዜ የልማት ዕቅድ ዝግጅት ታሳቢ በማድረግ የክፍያ መንገዶችን በማስፋፋት አሁን 301 ኪ.ሜ የሚሽፍነውን የክፍያ መንገድ ወደ 1650 ኪ.ሜ ለማድረስ እንዲሁም የማስተዳዳር አቅምን ለማሳደግ መሠራት እንደሚገባ ተነስቷል፡፡

በዚህም ዓመታዊ የትራፊክ ፍሰቱን ከፍ በማድረግ የሚሰበሰብን ገቢ በተገቢው መልኩ በማሳደግ የታለመለትን ግብ መምታት ይገባዋል፡፡

የኢንተርፕራይዙ ዋና ስራ እስኪያጅ የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ከድር በዕቅዱ ዙሪያ በየደረጃው አስፈላጊውን ግንዛቤ በመፍጠር እና በተለይም የመንግስት ሰራተኛው ሃገራዊ ዕቅዱ ዙሪያ ግልፅ ውይይት በማድረግ ለተግባራዊነቱ በይበልጥ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ሠራተኛውም በተሰማራበት የስራ መስክ በእውቀቱ እና በክህሎቱ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ሆኖ በመገኘት ውጤት ለማስመዝገብ በታላቅ ተነሳሽነት እንዲሁም ቁርጠኝነት ለውጡን ማስቀጠል እንደሚገባ አቋም በመያዝ ስብሰባው ተጠናቋል፡፡