ከ186 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ፡፡ የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭትን ለመቆጣጠር እንዲቻል መንግስት ዜጎች በቤታቸዉ እንዲቆዩ መወሰኑን ተከትሎ ሰራተኞችን ለማገዝ ያስችል ዘንድ ከ186 ሺህ ብር በላይ የሚገመት 95 ኩንታል የፉርኖ ዱቄት 372 ለሚሆኑ የጥበቃ እና የአካባቢ እንክብካቤ ሰራተኞች ሰጥቷል።