Top Stories

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝኤክስፕረስ ማይልስበሚል መጠሪያ ለደህንነት አምባሳደሮች ዕውቅና መስጠቱን ገለጸ።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ “ኤክስፕረስ ማይልስ” አዋርድ (ExpressMiles Award) በሚል መጠሪያ ለደህንነት አምባሳደሮች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል። የኢንተርፕራይዙ ኃላፊዎችና ሰራተኞች፤ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፤እንዲሁም ተሸላሚዎች የተገኙ ሲሆን የዕውቅና ፕሮግራሙ መዘጋጀቱ የመንገድ ደህንነትን ከማረጋገጥ አኳያ አዎንታዊ ሚና እንዳለው ጸገልጸዋል። በዕለቱ ሽልማቱን ያበረከቱት የኢንተርፕራይዙ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ...

read more

People & opinion

testimonials

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት

በሀገራችን በአይነቱ ልዩ የሆነውና በዓመት በአማካኝ አምስት ሚሊዮን የተሽከርካሪ ምልልሶችን የሚያስተናግደው የአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ አገልግሎት መስጠት ከጀመረባቸው ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ በመንገዱ ግራና ቀኝ ዳርቻዎች የሚካሄደው የችግኝ ተከላ እንቅስቃሴ መንገዱን ከሚጠቀሙት ተሽከርካሪዎች ብዛት አኳያ የሚመነጨውን የካርቦን ልቀትን ለመቆጣጠር የሚያግዝ በመሆኑ ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው በጎ ተግባር ነው፡፡

ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ (2008 – 2009 ዓም)

ሀገራችን በኢኮኖሚ እድገቷና በፀጥታዋ ተቻችሎ በመኖር እንዲሁም በብዙ ነገሮች ለሌሎች ሀገሮች ምሳሌ እየሆነች መጥታለች ፡፡ ሀገራችን አነስተኛ ተሽከርካሪ ካላቸው ሀገራት የምትመደብ ሆና ሳለ የሚደርሰው የትራፊክ አደጋ ግን ከፍተኛ ነው ፡፡ አሽከርካሪዎች በሚፈጥሩት ስህተት የራሳቸውንም ሆነ የሌሎችን ህይወት መቅጠፍ እንደሌለባቸው ተገንዝበው በየጊዜው የሚተላለፉ መልዕክቶችን ወደ ተግባር በመቀየር በፍጥነት መንገዱ ላይ ምንም አይነት አደጋ እንዳይደረስ አጋር እንዲሆኑና እንዲተባበሩ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ፡፡

ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል

የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት

የአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ በስኬታማ ጎዳና እየተጓዘ ያለውን የመንገድ መሰረተ ልማት ወደ አዲስና ከፍተኛ ደረጃ መሸጋገሩን ያበሰረ ታላቅ የልማት ፍሬ ነው፡፡ በመንገድ ግንባታውም አገራዊው አቅም ይበልጥ እያደገ መምጣቱን በግልፅ ያመላከተና በህዳሴው መስመር ህዝብና መንግስት በትብብርና ቅንጅት ከሰሩ ባደጉት አገራት የሚታዩ ድንቅ የእድገትና ሥልጣኔ ፍሬዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ምድር እውን ማድረግ እንደሚቻል ያሳየ የልማት ውጤት ነው፡፡

አ/ቶ ሙክታር  ከድር
መስከረም 7 2003 .

የአዲስ አዳማ ፈጣን መንገድ በዋናነት አዲስ የመንገድ ግንባታ ምዕራፍ የከፈተና እስካሁን ድረስ ከነበሩት መንገዶች ለየት ያለ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ነው፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ

ምቹና ዘመናዊ መንገዶች ከመውሰድና ማምጣት ባሻገር በአጭር ጊዜ በዝቅተኛ ወጪ ሕዝቦችን በማቀራረብ ገበያዎችን በማስተሳሰር ኢኮኖሚያዊ እድገትና ዘላቂ ልማትን ከማፋጠን ባሻገር የሀገርን መልካም ገፅታንም በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የሀገራችንን የመንገድ አውታር በዕጥፍ ለማሳደግ በመንግስት ትልቅ ግብ ተጥሎ እየተሰራ ሲሆን ሀገራችንም በመንገድ ግንባታ ሂደት ወደ አዲስ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

የቦርድ ሰብሳቢ መልዕክት
G.M Mustefa Abasimel
G.M Mustefa Abasimel

የዋ/ስ/አ/ መልዕክት የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አሁን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትን የአዲስ አበባ- አዳማ እና የድሬደዋ- ደወሌ እንዲሁም በቀጣይ ግንባታቸው የሚጠናቀቁ የክፍያ መንገዶችን የማስተዳደር፣ የመጠገን፣ የክፍያ መንገድ አገልግሎት የመስጠት እና ተጓዳኝ ስራዎችን የመስራት ኃላፊነት ተሰጥቶት፤ በብቃት እየተወጣ ያለ ተቋም ነው፡፡ አገልግሎት ሰጪ ተቋም የሆነው ኢንተርፕራይዙ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለአፍታም ያልተቋረጠ የ24/7 አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

read more
D.G.M Abiy Woretaw
D.G.M Abiy Woretaw

ETRE’S timeline in review… It all started with a dilemma whether to commence toll road operation with own staff or contract it out. A decision was made by the then Board Chair, now the Premier, to bestow trust on local youth to kick-start the first toll road operation within a month. Addis-Adama Expressway was the

read more

View The Big Picture on Instagram. Follow etre.com.et

ENKUTATASH

A post shared by Ethiopian Toll Roads (@etre.com.et) on

Featured Video

Recent Videos

1 2