የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጉብኝት በኢንተርፕራይዙ
ኢክመኢ / ETRE [ሚያዚያ /2017ዓ.ም] የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2014 በጀት ዓመት የመንገድ አስተዳደር ስርዓት ውጤታማነትን የክዋኔ ኦዲት በተመለከተ በኮሚቴው የተሰጡ የማስተካከያ ምክረ ሀሳቦች ላይ በኢንተርፕራይዙ በኩል የተተገበሩ የማስተካከያ ሥራዎችን 05 ሚያዝያ 2017 ዓ.ም ከፌዴራል ዋና ኦዲተር እና ከግዥ ባለስልጣን ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ገመገመ። በሂደቱም 3ቱን የድጋፍ እና ክትትል አግባቦች በመጠቀም በግኝቶቹ ላይ የተዘጋጁ ሪፖርቶችን በማዳመጥ የሪፖርቶቹን ትክክለኛነት የመስክ ምልከታ (ሱፐርቪዥን ) በማድረግ እንዲሁም በማጠቃለያው የአካል ግምገማ በማድረግ ከኢንተርፕራይዙ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል። በ2014 በጀት ዓመት ለኢንተርፕራይዙ የመንገድ አስተዳደር ስርዓት ውጤታማነትን ማረጋገጥን በተመለከተ ከተሰጡ 18 ግኝቶች መካከል 14 ግኝቶች ኢንተርፕራይዙ ማስተካከያ ያደረገ ሲሆን 4 ግኝቶችን ለማስተካከል በሂደት ላይ መሆኑ ተለይቷል። የፌዴራል ዋና ኦዲትር በግኝቶቹ ላይ የተወሰደዉ ማስተካከያ በጣም ጥሩ መሆኑንና የኢንተርፕራይዙ አመራሮች እና ሰራተኞች በቁርጠኝነት መስራታቸውን ያሳያል የሚል ሙያዊ