የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ከ1 ሺህ በላይ አጋዥ መፃሓፍት ድጋፍ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ከ1 ሺህ በላይ አጋዥ መፃሓፍት ድጋፍ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ03/07/2013 ዓ.ም ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ ለአቃቂ ወረዳ አስተዳደር ከ1 ሺህ በላይ አጋዥ መፃሓፍት ድጋፍ አደረገ፡፡

ኢንተርፕራይዙ ከሚሰጠው የክፍያ መንገድ አገልግሎት በተጨማሪ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ በአዲስ አበባ- አዳማ እና ድሬዳዋ- ደወሌ የክፍያ መንገዶች አቅራቢያ ለሚገኙ ማህበረሰቦች የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ወዘተ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት የማህበረሰቡን ችግር ከመፍታት እና ኑሮን ከማቅለል ረገድ የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ በመረዳት በአቃቂ ወረዳ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዋጋቸው ከ97 ሺህ ብር በላይ የሆነ፣ ከ1ኛ- 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚያገለግሉ እንዲሁም በሁሉም የትምህርት አይነቶች የተዘጋጁ አጋዥ መፃሓፍት ማበርከት ተችሏል፡፡

ኢንተርፕራይዙን በመወከል የርክክብ ስርዓቱን ያከናወኑት አቶ በላይ በየነ  ህብረተሰቡ የራሱ የሆነውን መንገድ እና የመንገዱን ሃብቶች በመጠበቅ እና በመንከባከብ ረገድ የድርሻውን እንዲወጣ በማለት፤ ተቋሙ ሁልጊዜም ከህብረተሰቡ ጎን እንደሚቆም ገልጸዋል፡፡

በርክክቡ ወቅት የተገኙት የወረዳው የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ፈጠነ በበኩላቸው ተቋሙ ያደረገው ድጋፍ ብቁ፣ ምክንያታዊ እና በሁሉ ረገድ ውጤታማ የሆነ ትውልድ ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት ከማገዝ ባለፈ ከማህበረሰቡ ጎን መቆሙን በተግባር ያሳየበት በመሆኑ አርዓያነቱ ከፍ ያለ ስለሆነ፤ ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል፡፡

 

 

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ

ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!