Shopping cart

ETRE

It is known that the Government of Ethiopia is undertaking vast and numerous developmental programs to achieve the Growth and Transformation Plan (GTP) series laid out for the holistic renaissance of the country. The Addis Ababa – Adama Expressway (AAE) is one of the construction mega projects developed as part of GTP-I which is open for traffic and administered by the Ethiopian Toll Roads Enterprise. Other expressways (Modjo-Hawassa and Adama-Awash) are underway and many more are planned for future development and operation in line with the dynamic socio-economic development of Ethiopia.

የኢ.ክ.መ.ኢ በአዲስ አዳማ የክፍያ መንገድ በጥበቃ አገልግሎት ተደራጅተዎ የጥበቃ አገልግሎት ለሚሰጡ ማህበራት የዕውቅና ሽልማት ሰጠ

  • Home
  • Uncategorized
  • የኢ.ክ.መ.ኢ በአዲስ አዳማ የክፍያ መንገድ በጥበቃ አገልግሎት ተደራጅተዎ የጥበቃ አገልግሎት ለሚሰጡ ማህበራት የዕውቅና ሽልማት ሰጠ

ኢክመኢ / ETRE [ጥቅምት 25/2017ዓ.ም]

በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የአዲስ አዳማ የክፍያ መንገድ 78ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የክፍያ መንገድ ሲሆን 21 የጥበቃ ማህበራትን በማደራጀት የደንበኞችን የጉዞ ደህንነት፣ የመንገድ ሃብት ደህንነት ለማስጠበቅ እና ፅዱና ምቹ የክፍያ መንገድ ለማድረግ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

በአዲስ አዳማ የክፍያ መንገድ በጥበቃ አገልግሎት ተደራጅተዎ በጥበቃ አገልግሎት እንዲሁም በመንገድ ፅዳት ላይ ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እና ለግንባር ቀደም የጥበቃ ማህበራት የዋንጫ እና የሰርተፊኬት ሽልማት አበረክቷል።

በዚህም ኢንተርፕራይዙ በተለያዩ መስፈርቶች ግንባር ቀደም ለሆኑ ለ3 የጥበቃ ማህበራት የዋንጫ ሽልማት፣ እንዲሁም በጥሩ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ለ10 የጥበቃ ማህበራት የሰርቲፊኬት እና በተለያየ ማህበር ውስጥ ለተደራጁ ጠንካራና ግንባር ቀደም ለሆኑ ለ4 ሴት ሰራተኞች የገንዘብ ሽልማት ከኢንተርፕራይዙ ተበርክቶላቸዋል፡፡

በክፍያ መንገዱ የጉዞ ደህንነት፣ የመንገድ ሃብት ጥበቃ እና የትራፊክ ደህንነት ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ እያደረጉ ለሚገኙ በኢንተርፕራይዙ ውስጥ ለተሰማሩ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለኦሮሚያ ፖሊስ፣ ለኦሮሚያ ትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም በክፍያ መንገዱ የመንገድ ደህንነት እና ትራፊክ ቁጥጥር ቡድን የሰርቲፊኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የኢንተርፕራይዙ ዋና ስራ እሰፈፃሚ አቶ ሙስጠፋ አባሲመል እንዳሉት የተሰራው ስራ የሚያስመሰግን እና የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው በክፍያ መንገዱ ውስጥ የተሰማሩ የጥበቃ ማህበራት በቀጣይ በትጋት መሰራት እንዲሁም መንገዱን ነቅተው መጠበቅ እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!

☎️ 0114171717 /00/13 8808
www.etre.com.et
Facebook: https://www.facebook.com/etre01
Telegram: https://t.me/etrechannel
YouTube: youtube.com/@ETRE001
https://www.tiktok.com/@etre2007

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked*