ኢክመኢ / ETRE [ጥቅምት 19/2017ዓ.ም]
ኢንተርፕራይዙ በሶስቱም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች (በአዲስ – አዳማ፣ በድሬደዋ – ደዋሌ እና በሞጆ – ባቱ የክፍያ መንገድ) በሐገራችን የ2017 በጀት ዓመት የ100 ቀናት የሪፎርምና ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ በየዘርፉ የተከናወኑ ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር በማቅረብ ውይይት ተደርጎበታል።
በተጨማሪም የኢንተርፕራይዙ የመጀመሪያ የሶስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የኢንተርፕራይዙ በ2017ዓ.ም ተግባራዊ የሚሆነው ተቋማዊ መዋቅርን አስመልክቶ በሰራተኞች ድልድል እና ምደባው ኮሚቴ ትግበራውን አስመልክቶ ገለፃ እና ውይይት አድርጓል።
በመጨረሻም በኢንተርፕራይዙ ተግባራዊ እየተደረጉ በሚገኙ የጥራት አስተዳደር ስርዓት (Quality Management System QMS ISO 9001)፣ Road Traffic Safety (RTS) ISO 39001 እና Occupational Health and Safety (OH&S) ISO 45001 አስመልክቶ ገለፃ እና ውይይት ተደርጓል።
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!
0114171717 /00/13 8808
Facebook: https://www.facebook.com/etre01
Telegram: https://t.me/etrechannel
YouTube: youtube.com/@ETRE001