ኢክመኢ / ETRE [ህዳር 17/2017ዓ.ም]
ህዳር 16/2017ዓ.ም በአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ አቅጣጫ እየተጓዙ እያሉ በኪ.ሜ8 ላይ 2 ሰው የጫነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርከሪ እና 14 ሰው የጫነ ዶልፊን ሚኒባስ ተሽከርካሪ ጋር በደረሰው የመጋጨት አደጋ 1 የሞት አዳጋ መድረስ ችሏል።
በክፍያ መንገዱ ከ136 ቀናት በኋላ የደረሰ የሞት አደጋ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያዉ የሞት አደጋ ሆኖ ተመዝግቧል። በአጠቃላይ ሞት 1፣ ከባድ የአካል ጉዳት 2፣ቀላል የአካል ጉዳት 7 በድምሩ 10 በሰዉ ላይ ጉዳት እና በኢንተርፕይዙ ንብረት ላይ ጉዳት መድረስ ችሏል።
ኢንተርፕራይዙ ደንበኞች በፍጥነት መንገዱ ውስጥ በሚያሽከረክሩበት ወቅት በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩ እያሳሰበ፣ የትራፊክ አደገን ለመቀነስ የበኩላችንን አስታፆ እናድርግ እያለ የዘውትር መልዕክቱን ያስተላልፋል።
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!
☎️ 0114171717 /00/13 8808
www.etre.com.et
Facebook: https://www.facebook.com/etre01
Telegram: https://t.me/etrechannel
YouTube: youtube.com/@ETRE001
https://www.tiktok.com/@etre2007