የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በቢሾፍቱ ከተማ “እኩልነት እና ሕብረብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት፤ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል ሰፊ ውይይት በማድረግ በድምቀት ተከብሯል፡፡
በዕለቱ የኢንተርፕራይዙ ዋ/ስ/አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ አባሲመል አገራዊ ሪፎርሙ ለጠንካራ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያበረከተውን አስተዋጽኦ በማንሳት ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በህገ መንግስት የተቀመጠውን መብት ከመጠሪያ ባለፈ መተግበር የጀመሩበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የኢንተርፕራይዙ ም/ዋ/ስ/አስኪያጅ አቶ አብይ ወረታው የህወሃት ኢ-ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴ እና ፌደራላዊ ስርዓቱን ለማዳን የተከናወኑ ተግባራት ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡ ቤቱም የቀረቡ ገለፃዎችን እንደመነሻ በመውሰድ ሰፊ ውይይት አካሄዷል፡፡
በውይይቱም መንግስት በህገወጡ የህወሃት ቡድን ላይ የወሰደው እርምጃ ተገቢ መሆኑን በማንሳት፤ አገር ለማፍረስ የተቃጣውን ሴራ ለማክሸፍ የተደረገው ህግ የማስከበር ዘመቻ ትክክለኛ እና ወቅቱን ያገናዘበ በመሆኑ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች እኩልነት እና ሕብረብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለጋራ ብልፅግና መትጋት እንደሚገባ መግባባት ላይ በመድረስ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!
ETRE
April 11, 2023የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
ETRE
April 11, 2023የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ