========================
ኢክመኢ / ETRE [ታህሳስ 24/2017ዓ.ም]
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራዊ ኮንፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው የ2017 ዓ.ም የበጋ ወራት የተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ለውድድሮቹ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች፣ የስፖርተኞች ምልመላ እና የመለማመጃ ቦታዎች የቅድመ ዝግጅት ስራዉን አጠናቆ ታህሳስ 27/2017ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ በሚደረገው የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ቅድመዝግጅቱን አጠናቋል።
የስፖርት ጤና ቡድን ኮሚቴ አባላት በሁሉም የስፖርት ዘርፎች የቀረበውን የስፖርት ትጥቅ አበርክተዋል። የስፖርት ጤና ቡድን ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የበላይ ጠባቂ የሆኑት አቶ ናስር አደም “በ2016ዓ.ም በተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ያስመዘገብነውን ውጤት የበለጠ ለማጠናከር መትጋት አለብን” የሚል መልዕክት አስተላልፏል።
ኢንተርፕራይዙ ከ2015ዓ.ም ጀምሮ ለ2 ዓመታት በተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ሲሳተፍ የቆየ ሲሆን በአጠቃላይ በተሳተፈባቸው ሁለት ዓመታት 5 ዋናጫዎችን እና ሜዳሊያዎችን ማሳካት ችሏል።
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!
☎️ 0114171717 /00/13 8808
www.etre.com.et
Facebook: https://www.facebook.com/etre01
Telegram: https://t.me/etrechannel
YouTube: youtube.com/@ETRE001
https://www.tiktok.com/@etre2007