ኢክመኢ / ETRE [ሚያዚያ /2017ዓ.ም]
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2014 በጀት ዓመት የመንገድ አስተዳደር ስርዓት ውጤታማነትን የክዋኔ ኦዲት በተመለከተ በኮሚቴው የተሰጡ የማስተካከያ ምክረ ሀሳቦች ላይ በኢንተርፕራይዙ በኩል የተተገበሩ የማስተካከያ ሥራዎችን 05 ሚያዝያ 2017 ዓ.ም ከፌዴራል ዋና ኦዲተር እና ከግዥ ባለስልጣን ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ገመገመ።
በሂደቱም 3ቱን የድጋፍ እና ክትትል አግባቦች በመጠቀም በግኝቶቹ ላይ የተዘጋጁ ሪፖርቶችን በማዳመጥ የሪፖርቶቹን ትክክለኛነት የመስክ ምልከታ (ሱፐርቪዥን ) በማድረግ እንዲሁም በማጠቃለያው የአካል ግምገማ በማድረግ ከኢንተርፕራይዙ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል።


በ2014 በጀት ዓመት ለኢንተርፕራይዙ የመንገድ አስተዳደር ስርዓት ውጤታማነትን ማረጋገጥን በተመለከተ ከተሰጡ 18 ግኝቶች መካከል 14 ግኝቶች ኢንተርፕራይዙ ማስተካከያ ያደረገ ሲሆን 4 ግኝቶችን ለማስተካከል በሂደት ላይ መሆኑ ተለይቷል።
የፌዴራል ዋና ኦዲትር በግኝቶቹ ላይ የተወሰደዉ ማስተካከያ በጣም ጥሩ መሆኑንና የኢንተርፕራይዙ አመራሮች እና ሰራተኞች በቁርጠኝነት መስራታቸውን ያሳያል የሚል ሙያዊ አስተያየት በመስጠት አመራሮችን እና ሰራተኞችን አመስግኗል።
ከነበሩ የኦዲት ግኝቶች መካከል ማሻሻያ የተደረገባች፡
- በኢንተርፕራይዙ መንገዶች ላይ የሚደረጉ የመንገድ ጥገና፣
- ጽዳትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን በሚያከናውኑበት ወቅት ከአደጋ የተጠበቀ የስራ ክልል (Work Zone Traffic Control) በመተግበር መጀመሩ ፤
- ለሠራተኞች የደህንነት መጠበቂያ አልባሳት መሟላቱ ፤
- ከክብደት በላይ ጭነው ወደ ክፍያ መንገዱ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱ እና ተግባራዊ መደረጉ ፤
- ዘመናዊ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ስርዓት መዘርጋቱ ፤
- በመንገድ ሀብቱ ላይ የሚደርሰውን ጉዳትና ብልሽቶችን በወቅቱ መጠገን መጀመሩ ፤
- ጉዳት የደረሰባቸውን ንብረቶች በዕቃ መረከቢያ ሰነድ ገቢ ማድረግ መጀመሩ እና እንደ አይነታቸውና መጠናቸው ተለይቶ መቀመጣቸው ፤
- የኤሌክትሮ መካኒካል ወርክ ሾፕ መቋቋሙ ፤
- የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችና የነዳጅ ማደያ ግንባታ ማለቃቸው ፤
- ኢንተርፕራይዙ የሚጠቀምባቸውን ተሸከርካሪዎች በዘመናዊ ሁኔታ መቆጣጠር መጀመሩ፤
- ተቋማዊ መዋቅር ተዘጋጅቶ ተግባራዊ መደረጉ ፤
- ለኦፕሬሽን የሚወጡ ወጪዎችን ወጪ ቆጣቢ የሆነ ስርዓት በመዘርጋት በተለይ የትርፍ ሰዓት ክፍያና የነዳጅ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ፤
- በመንገድ ሃብቱ ላይ ጉዳት አድረሰው ከጉዳት አድራሹ በወቅቱ መሰብሰብ የነበረበት ነገር ግን በወቅቱ ያልተሰበሰበ 11,192,840.75 ብር ውስጥ 90 ፐርሰንት መሰብሰቡ ፤
- የክፍያ መንገድ ተጠቃሚ ደንበኞች በንብረት ካሳ ግምት ላይ ቅሬታ ካቀረቡበት ቀን ጀምሮ በ8.5 ቀናት ውስጥ ውሳኔ ማግኘቱ ፤
ከነበሩ የኦዲት ግኝቶች መካከል ተጨማሪ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው
- በድሬደዋ ደወሌ ክፍያ መንገድ ስራ በጀመረበት ወቅት ወጥ የሆነ የመንገድ ርክክብ ማድረጉንና ቆጠራ መደረጉን ማረጋገጥ ፤
- ኢንተፕራይዙ በአዲስ አዳማ ፍጥነት መንገድ ላይ የሚገኙ የመንገድ ሀብቶችን ለማስጠበቅ ከ21 ማህበራት ጋር የጥበቃ ውል ስምምነት በመግባት በየወሩ የደመወዝ ክፍያ ብር 381,429.00 የሚከፍል ቢሆንም በየጊዜው የመንገድ ሃብቶች ስርቆት እየተፈጸመ መቀጠሉ ፤
- ኢንተርፕራይዙ የሚጠቀምበት የግዥ መመሪያ በቀጣይ ቶሎ ማጸደቅ አለመቻሉ፤
- በድሬዳዋ ደወሌ ክፍያ መንገድ ቅርንጫፍ መ/ቤት ተጨማሪ የፋይናንስ ምንጮችን ከመፍጠር አኳያ ማሻሻያ ቢደረግባቸው የሚል ሃሳቦች ተነስቷል።




የኢንተርፕራይዙን የዋና መ/ቤት የትራፊክ መቆጣጠሪያ ክፍል፤ የችግኝ ማፊያ ቦታ፤ የንብረት ማከማቻ ክፍል፤የኤሌክትሮ መካኒካል ይጥገና ማዕከል እና የተሽከርካሪ ጥገና መስሪያ ቦታዎች ፤ የኪ.ሜ 29 የአገልግሎት መስጫ ጣቢያ፤ የድሬደዋ ደወሌ ክፍያ ጣቢያ እንዲሁም የአዲስ አዳማ ቅርንጫፍ መ/ቤት ጉብኝት ያደረጉ መጎብኘት ችሏል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ደረጀ ደበላ ኢንተርፕራይዙ ራሱን ለተገልጋይ እና ባለድርሻ አካላት በአግባቡ መሸጥ እንዳለበት እና ለፖርላማ ቋሚ ኮሚቴ ስለ ኢንተርፕራይዙ የተሻለ ግንዛቤ መስጠት እንዳለበት ገልፃል። በቀጣይ የመንገድ ውበት ላይ ብዙ ስራ መሰራት እንዳለበት፤ እንዲሁም የፖርላማ አባላት በቀጣይ የችግኝ ተከላ መርሃግብር በክፍያ መንገዱ እንዲያደርጉ ቦታ በመምረጥ፤ ኢንተርፕራይዙን ለመደገፍ የአዋጅ እና ደንብ ማሻሻያዎችን ትኩረት መደረግ እንዳለበት እና የኢንተርፕራይዙ የውስጥ ኦዲት ትኩረት ተሰጥቶት በሰው ኃይል እና በስልጠና መጠናከር እንደሚገባ እና የውስጥ አሰሪር ማንዋሎች በአግባቡ መተግበራቸውን በውስጥ ኦዲት ማረጋገጥ ለኢንተርፕራይዙ ቀጣይነት የጀርባ አጥንት በመሆናቸው ትኩረት ተደርጎ ሊጠናከሩ እንደሚገባ አመላክቷል።
በጉብኝቱም ብዙ አበረታች ነገሮችን መታዘባቸውን እንዲሁም ኢንተርፕራይዙ ላደረገላቸው ዝግጁነቶች እና መልካም የሆነ አቀባበል የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ደረጀ ደበላ ለኢንተርፕራይዙ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ምስጋና አቅርቧል።
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!