Shopping cart

ETRE

It is known that the Government of Ethiopia is undertaking vast and numerous developmental programs to achieve the Growth and Transformation Plan (GTP) series laid out for the holistic renaissance of the country. The Addis Ababa – Adama Expressway (AAE) is one of the construction mega projects developed as part of GTP-I which is open for traffic and administered by the Ethiopian Toll Roads Enterprise. Other expressways (Modjo-Hawassa and Adama-Awash) are underway and many more are planned for future development and operation in line with the dynamic socio-economic development of Ethiopia.

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

  • Home
  • News
  • የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

‎ኢክመኢ[ETRE ጥቅምት 11/2019 ዓ/ም]

​የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። በግምገማ መድረኩ ባለፉት ሦስት ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተመዘገቡ ስኬቶች እና የታዩ ክፍተቶች በሰፊው ተመልክተዋል።

​በመድረኩ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች እና የቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸም አቅርበው የተገመገሙ ሲሆን፤ ለቀጣይ ሥራዎች ዋና ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች ተለይተዋል፡-

​-የክፍያ መንገዶችን ጥራትና ደህንነት ማረጋገጥ

​-ለጉዞ አድራጊዎችና ለመንገድ ተጠቃሚዎች የላቀና ፈጣን አገልግሎት መስጠት

​-የተቋሙን ገቢ ማሳደግ

​-የሕዝብ ሀብት በአግባቡና በቁጠባ ጥቅም ላይ መዋሉን ማረጋገጥ

​በአጠቃላይ ግምገማው የተቋሙን አገልግሎት ጥራት፣ ውጤታማነት እና አጠቃላይ አቅም ይበልጥ ለማሳደግ ጠንካራ መሠረት የሚጥል ሆኖ ተጠናቋል።

​በግምገማው ላይ አቅጣጫ ያስቀመጡት የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙስጠፋ አባሲመል፤ የተቋሙን ዕቅዶች በብቃት በመፈጸም፣ የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችን በማስቀጠል እና ክፍተቶችን በወቅቱ በማረም የተሻለ ተቋማዊ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ

“ደኅንነትዎ የክብር ስማችን ነው!!”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked*