ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የመጡ ጐብኚዎች ኢንተርፕራይዙን በመጐብኘታቸው ምርጥ ተሞክሮ እንዳገኙ ተናገሩ!!

ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የመጡ ጐብኚዎች ኢንተርፕራይዙን በመጐብኘታቸው ምርጥ ተሞክሮ እንዳገኙ ተናገሩ!!

በመስከረም 2010 ዓ.ም ከቶጐ፣ ዛምቢያ እና ካሜሩን የተውጣጡ ከ40 በላይ የሚሆኑ ጐብኚዎች በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ጉብኝታዊ ስልጠና አካሄዱ፡፡

የኢንተርፕራይዙን አጠቃላይ ገፅታ በምስል የተደገፈ ገለፃ እንዲሁም የደህንነት መቆጣጠሪያ ክፍሎች፣ የክፍያ ጣቢያዎች፣ የክብደት መቆጣጠሪያ ሚዛኖችና የመንገዱን የተለያዩ ክፍሎች በተግባር የታገዘ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝቱም ዘመናዊ የመንገድ አስተዳደር በኢትዮጵያ ምን ያህል ደረጃ እንደተጓዘ፣ የክፍያ መንገድ አገልግሎት አሰጣጥ ምን እንደሚመስል፣ የመንገድ ደህንነት ሁኔታ ለመቆጣጠር የተሰሩ ስራዎች እነዲሁም አጠቃላይ ገፅታውን በተመለከተ ተሞክሮ ማግኘታቸውንና፤ ወደ ሃገራቸውም ሲመለሱ ያገኙትን ልምድ በማካፈል በዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚተጉ ተናግረዋል፡፡