የአዲስ – አዳማፈጣንመንገድ

የአዲስ አበባ-አዳማ መንገድ የሀገራችን ዋነኛ የወጪ እና ገቢ ንግድ መስመር የሆነው አዲስ አበባ-አዋሽ-ሚሌ-ጋላፊ (ጂቡቲ) እንዲሁም ከደቡብ የሀገራችን ክፍል የሚያገናኘው የአዲስ-ሞጆ -አዋሳ-ሞያሌ (ሞምባሳ) እና ከምስራቁ የሀገራችን ክፍል ጋር የሚያገናኘው የአዲስ-አዋሽ-ሐረር-ጅጅጋ-ቶጎጫሌ (በርበራ) ኮሪደሮች አካል እንደመሆኑ መጠን ከሁሉም የሀገራችን አውራ መንገዶች የበለጠ ከፍተኛ ትራፊክ በየዕለቱ የሚስተናገድበት ነው፡፡ ይህም ከአዲስ አበባ – ዱከም – ቢሾፍቱ – ሞጆ – አዳማ ከተሞችን የሚያገናኝ ሆኖ ምስራቁ የሀገራችንን ክፍል የሚይዝ ሲሆን ከአዲስ አበባ ላይ ተነስቶ አዳማ ከተማ መውጫ ላይ ወደ ወለንጪቲ የሚወስደውን መንገድ ያገናኛል፡፡ ከመጋቢት 2002 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የመንገዱ ግንባታ ተጠናቆ በመስከረም 2007 ለትራፊክ ክፍት ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቀጣዩ የአዳማ-አዋሽ የመጀመሪያ ምእራፍ 60 ኪ.ሜ በግንባታ ላይ ይገኛል።