ከአፍሪካ፣ ከእስያና ከአውሮፓ የተለያዩ 27 ሀገራት የተውጣጡ በርካታ ተሣታፊዎች ኢንተርፕራይዙን ጎበኙ፡፡

ከአፍሪካ፣ ከእስያና ከአውሮፓ የተለያዩ 27 ሀገራት የተውጣጡ በርካታ ተሣታፊዎች ኢንተርፕራይዙን ጎበኙ፡፡

በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ለ5 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የ17ኛው የሌበር ቤዝድ ፕራክቲሽነር አህጉራዊ ጉባዔ አንድ አካል የነበረው ጉብኝት በኢንተርፕራይዙ ተካሂዶ ውሏል፡፡ ከአፍሪካ፣ ከእስያና ከአውሮፓ የተለያዩ 27 ሀገራት የተውጣጡ በርካታ ተሳታፊዎች ኢንተርፕራይዙን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱም አጠቃላይ ስለ ኢንተርፕራይዙ ገፅታ ገለፃ የተደረገ ሲሆን በማስከተልም በፍጥነት መንገዱ ላይ ስላለው የደህንነት ሁኔታና ምን ያህል ቴክኖሎጂ በመንገዱ ላይ ተግባራዊ እንደተደረገ ለማሳየት ተችሏል፡፡ እንዲሁም የደህንነት መቆጣጠሪያ ክፍል(monitoring room) የጎበኙ ሲሆን በዚህም ኢትዮጵያ በመንገድ ልማት ዘርፍ ምን ያህል እንደተጓዘች ማሳያ ነው ብለዋል፡፡