ኢንተርፕራይዙ አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ መጠን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሻሻል ለደንበኞቹ ምቾትና ደህንንት ትኩረት በመስጠት ገቢውን በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ቀዳሚ ጉዳዩ ነው፡፡ በዚህ ሂደትም የመንገዱ ብሎም የሀገር ሀብት የሆኑ የመንገዱ ልዩ ልዩ ንብረቶችን በመጠበቅ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በማስተዋወቅ እንዲሁም ውብና ማራኪ አካባቢን በመፍጠር የተሸከርካሪው ደህንነትና ምቾት እንዲጠበቅና የተሸለ አገልግሎት አሰጣጥ መፍጠር ይጠበቅበታል፡፡

መንገዱን ውብና አረንጓዴ ለማድረግ በየክፍያ ጣቢያዎቹ ለሚፈለገው የውሃ አገልግሎት ቀደም ሲል ከአቃቂ ቃሊቲ በሶስት የውሃ ቦቴ ተሸከርካሪ አማካኝነት ከሚያገኘውን የውሃ አቅርቦት በተጨማሪ በመንገዱ ኪሎ ሜትር 22 ላይ 4.6 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎ የከርሰ ምድር ውሃ ማበልፀግ ስራ አከናውኗል፡፡

 

Add Comment