Version | |
Download | 0 |
Stock | ∞ |
File Size | 4.00 KB |
Create Date | March 12, 2020 |
Download |
የጨረታ ማስታወቂያ
ግ.ጨ.ቁ 35/2012
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን አቅርቦት ፍላጎት ካላቸው የሃገር ውስጥ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል.
- የሰራተኞች ዩኒፎርም፣ ጃኬት፣ እና ሸሚዝ ግዥ
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይኖርባቸዋል
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ
- የታክስ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ 90 ( ዘጠና ) ቀናት
- የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 30,000 (ሰላሳ ሺ) ብር ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያው በሲ.ፒ.ኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል
- ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱ በሚገኝበት በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤት በግዥ ክፍል ቢሮ. ቁጥር 01 የማይመለስ 100.00( አንድ መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን እና ሰዓት
21 / 07 / 2012 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት
- ጨረታው የሚከፈተው፡- በዕለቱ 21 / 07 / 2012 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለበለጠ መረጃ እና ማብራሪያ ዋናው መስሪያ ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 0114171703 መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ (ዋና መስሪያ ቤት ቱሉ ዲምቱ)