የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የሥራ አመሪር ቦርድ የኢንተርፕራይዙን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ገምግሞ አጸደቀ።
================================ ኢክመኢ [ETRE ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም] አብዛኛዎቹ የቦርዱ አባላት በቅርቡ በአዲስ መልክ የተመደቡ በመሆናቸው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ተመድበው የመጡት ከፍተኛ ባለሙያዎች በቦርድ አስተዳደር መመሪያ ላይ አጭር ስልጠና ለቦርዱ አባላት የሰጡ ሲሆን፣ በመቀጠልም የቦርዱ ሰብሳቢ የተከበሩ ክቡር ዶ/ር ተሾመ አዱኛ ለዕለቱ የተያዘውን አጀንዳ በማስጸደቅ መደበኛ ስብሰባውን አስጀምረዋል

