አቶ ሙስጠፋ ከድር ፡በመንገዱ ዙሪያ ላይ ችግኝ መትከል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል

አቶ ሙስጠፋ ከድር ፡በመንገዱ ዙሪያ ላይ ችግኝ መትከል  አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ ከድር እንደተናገሩት በፍጥነት መንገዱ የሚካሄደው የአካባቢና የአረንጓዴ ልማት ዋነኛው ዓላማ ለመንገዱ ተጠቃሚዎች መንገዱን ምቹና ውብ ከማድረግ ባሻገር የአካባቢውን የአየር ንብረት ለአካባቢው ነዋሪዎችና ለመንገዱ ተጠቃሚዎች ተስማሚ ለማድረግ እንዲሁም የካርበን ልቀትን የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ችግኞችን የመትከልና የማፅደቅ ስራዉ የመንገዱ ተጠቃሚዎች በምሽት ሲያሽከረክሩ ከተቃራኒ አቅጣጫ የሚመጣውን መብራት በመከላከል የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ እንዲችሉ ለማድረግ ነው፡፡