በአዲስ አበባ – አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

በአዲስ አበባ – አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

በአዲስ አበባ – አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ በ120 ሚሊየን ብር የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለመገንባት ነሐሴ 21/2009 ዓ.ም የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡  

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት መስከረም 4/2007 ዓ.ም ጀምሮ ለአፍታም ያልተቋረጠ የ24/7 የክፍያ መንገድ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

ኢንተርፕራይዙ የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ ከኦሮሚያ የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በፈጣን መንገዱ ኪ.ሜ 29 ላይ በሁለቱም አቅጣጫ የሚገነባው የተለያየ አገልግሎት የሚሰጠው ግንባታ ፕሮጀክት ተጠቃሽ ነው፡፡

በኦሮሚያ ክልል ፈንድ አድራጊነት ተገንብቶ አገልግሎት የሚሰጠው ተቋም  የአካባቢውን ህብረተሰብ  ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት ሲጀምርም ከ600 በላይ ወጣቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይታመናል፡፡

120ሚሊየን ብር የሚፈጀው ይህ አገልግሎት ሰጭ ተቋም ግንባታው ተጠናቆ ሲያልቅ ለመንገዱ ተጠቃሚዎችና ለአካባቢው ህብረተሰብ  የነዳጅ ማደያ፣ የጋራዥ፣ የሬስቶራንት፣ የሱፐርማርኬት እንዲሁም የእንግዳ ማረፊያና የመሳሰሉ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡