በሁለቱም አቅጣጫ የሚገነቡት አገልግሎት ሰጪ ጣቢያዎች ሲጠናቀቁ ለአካባቢው ህብረተሰብ የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ተነገረ

በሁለቱም አቅጣጫ የሚገነቡት አገልግሎት ሰጪ ጣቢያዎች ሲጠናቀቁ ለአካባቢው ህብረተሰብ የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ተነገረ

በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ኪ.ሜ 29 ላይ በሁለቱም አቅጣጫ የሚገነቡት አገልግሎት ሰጪ ጣቢያዎች የመሰረት ድንጋይ በተቀመጠበት ነሐሴ 21/2009 ዓ.ም ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ም/ዋ/ስ/አስኪያጅ ኢንጂነር አብይ ወረታው እንደተናገሩት፡-

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ግንባታቸው የተጠናቀቁ የክፍያ መንገዶችን  ለማስተዳደር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 843/2006 እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 310/2006 የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡

ኢንተርፕራይዙ ላለፉት ሦስት ዓመታት የ24/7 የክፍያ መንገድ አገልግሎት በመስጠት ከ15 ሚሊየን በላይ የተሽከርካሪዎች ምልልስን ያስተናገደ ሲሆን በዚህም ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ለመሰበስብ ተችሏል፡፡

በ2010 የውጤት ተኮር በጀት ዓመታዊ ዕቅድ ከሚገነቡ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው በቀን ከ20 ሺ በላይ የተሸከርካሪዎች ምልልስ የሚስተዋልበት የአዲስ አበባ – አዳማ የፍጥነት መንገድ የተጠቃሚዎችን ፍላጐት ለማርካት የሚገነቡት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ 120 ሚሊየን ብር በፈጀ ወጪ የሚገነባው ተቋም የነዳጅ ማደያ፣ ጋራዥ፣ ሬስቶራንት፣ ሱፐርማርኬት፣ እንግዳ ማረፊያ የመሳሰሉትን በመያዝ ሁለገብ አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡