የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2010 የሰንደቅ ዓላማ በዓል አከበረ

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2010 የሰንደቅ ዓላማ በዓል አከበረ

በሀገር ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ “ራዕይ ሰንቀናል ለላቀ ድል ተነስተናል” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የሠንደቅ ዓላማ ቀን የኢንተርፕራይዙ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በፓናል ውይይትና በሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ስነ-ስርዓት ተከብሯል፡፡ በፓናል ውይይቱም  “የኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና ሀገራዊ ህዳሴ” በሚል ረዕስ በቀረበው ሰነድ ላይ የተወያዩ ሲሆን ሀገሪቱ እያስመዘገበች ላለው ዕድገት መሰረቱ የሀገር አንድነት በመሆኑ ለሰንደቅ ዓላማ ጥልቅ ፍቅርና ክብር መስጠት ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዕለቱም ቃለ መሃላ የመፈፀም ስነ ስርዓቱ የበዓሉ ማጠቃለያ ሆኗል፡፡