የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ3ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበር

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ3ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበር

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የተመሰረተበትን 3ተኛ ዓመት ጥቅምት 18_02_2010 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በድምቀት አክብሯል፡፡

በእለቱም የኢንተርፕራዙ ቦርድ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የኢንተርፕራይዙ ሰራተኞችና አመራሮች የተገኙ ሲሆን በ 2009 ዓ.ም የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞች እንዲሁም ከኢንተርፕራይዙ ጋር በቅርበት ሲሰሩ ለነበሩ አጋር ድርጅቶች የእውቅና የምስክር ወረቀትና ልዩልዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል፡፡

ይህ በያመቱ የሚደረገው የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ሰራተኞችን ከማበረታታትና የስራ ጥራትን ከማምጣት አንፃር ትልቅ ድርሻ እንዳለውም ተገልፆዋል፡፡