የኢንተርፕራይዙ የመንገድ ደህንነት ቡድን የተሽከርካሪዎች ደህንነት ምርመራ ማድረጉ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቀነስ እንደሚረዳ ተገለፀ፡፡

የኢንተርፕራይዙ የመንገድ ደህንነት ቡድን የተሽከርካሪዎች ደህንነት ምርመራ ማድረጉ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቀነስ እንደሚረዳ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገደች ኢንተርፕራይዝ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በወር አንድ ጊዜ በተለያዩ የክፍያ ጣቢያዎች በመግቢያ በሮች ላይ አነስተኛ የተሸከርካሪ ደህንነት ምርመራ ያደርጋል፡፡

በዚህም ምርመራ በግልፅ የሚታዩ ቀላልና ነገርግን ለከፍተኛ ጉዳት የሚዳርጉ ቀበቶ አለማሰር፣ ፍሬቻ መብራት አለመስራት ፣ የዝናብ መጥረጊያ ላይ ችግር መኖርና የመሳሰሉትን በመለየት የዚህ ዓይነት ችግር ያለባቸውን አሽከርካሪዎች ወደ መንገዱ እንዳይገቡ በማድረግና መቀጣት ያለባቸውን አሽከርካሪዎች ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር የእርምት እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የመንገድ ደህንነት ቡድን መሪ አ/ቶ አብዱረዛቅ ሙባረክ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ይህ ፍተሻ መደረጉ በመንገዱ ውስጥ ለሚከሰቱ አደጋዎች ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ እንዲሁም የሰውና የንብረትን አደጋ ለመታደግ እንደሚረዳ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡