በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የITS አለም አቀፍ ተሞክሮ አስመልክቶ ሴሚናር ተካሄደ

በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የITS አለም አቀፍ ተሞክሮ አስመልክቶ ሴሚናር ተካሄደ

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ባመቻቸው በዚህ ሴሚናር ላይ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች መዳቢ ኤጀንሲ ከመንገዶች ባለስልጣን እንዲሁም ከኢንተርፕራይዙ ለተወጣጡ ባለሞያዎችና አመራሮች የ ITS (Intelligent Transportation System) (ዘመናዊ የትራንስፖርት ስርዓት) አለም አቀፍ ተሞክሮ ላይ ውይይት ተካሂዷል ፡፡

በውይይቱ ላይ የ ITS መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳቦች የአሜሪካና የኮሪያ አለም አቀፍዊ ልምዶች በተወካዮቻቸው አማካኝነት ቀርቧል ፡፡

ITS የትራንስፖርት ዘርፉን ቀልጣፋ ዘመናዊና የተሳሰረ በማድረግ ሀገራዊ የትራንስፖርት ደረጃን ከፍ በማድረግና በመረጃ በማስተሳሰር በኩል የሚኖረው ድርሻ የጎላ ነው ፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ስራው ከጀመረ 25 ዓመት ያልሞላው ይህ ዘርፍ በሀገራችን በየደረጃው ጅማሬዎች ቢኖሩም በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠልና በሀገር ደረጃ ለሚደረገው ከፍተኛ ለውጥ ከአመራሩ ጀምሮ በዘርፉ ያሉ ሞያተኞች በቅንጅት መስራታቸው አስፈላጊ መሆኑ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል ፡፡

ከኢትዮጵያ ደረጃዎች መዳቢ ኤጀንሲና ከመንገዶች ባለስልጣን የመጡት ተወካዮች ከኢንተርፕራይዙ ጋር በቅንጅት ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡