የኢንተርፕራይዙ የመንገድ ደህንነት ቡድን የተሽከርካሪ ደህንነት ምርመራ አደረገ

የኢንተርፕራይዙ የመንገድ ደህንነት ቡድን የተሽከርካሪ ደህንነት ምርመራ አደረገ

ኢንተርፕራይዙ የተሽከርካሪዎችን የፍጥነት ወሰን ለመቆጣጠር የራዳር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ እያደረገ ነው ፡፡

የፍጥነት ወሰንን ጠብቆ አለማሽከርከር ለአደጋ መንስኤ እንዲሁም መባባስ እንደ ምክንያት ከሚጠቀሱ ነገሮች የመጀመሪያ ቦታውን ይይዛል ፡፡ የመንገድ ደህንነትን ለማስጠበቅ እና የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቀነስ ግንዛቤ ከማስያዝ ጀምሮ ህግ እና ደንቦችን በመቅረፅ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ፡፡

የአዲስ አበባ-አዳማ የፍጥነት መንገድ በቀን ከሃያ ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን እንደማስተናገዱ በመንገዱ ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን

ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ ይገኛል ፡፡ ከዚህም ውስጥ የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያ (ራዳር) ተግባራዊ መሆን ተጠቃሽ ነው ፡፡

የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቀነስ በፍጥነት መንገዱ የተለያዩ ክፍሎች ተንቀሳቃሽ የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያ በመጠቀም ክትትል ይደረጋል ነው ፡፡ በዚህ መሰረት የፍጥነት ወሰን ጠብቀው በማያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ላይ የማስተማር እና የ

እርምት እርምጃ እየተወሰደ ነው ፡፡

የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ፖሊሶች ከአዲስ -አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ ከተወሰነዉ የፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከረክሩ የነበሩ አሽከርካሪዎችን ትምህርት  እየሰጡ ነዉ፡፡