በቀን 01/05/2018 ከፍተኛ ገቢና ፍሰት የተመዘገበበት ቀን ሆኖ ውሏል፡፡

በቀን 01/05/2018 ከፍተኛ ገቢና ፍሰት የተመዘገበበት ቀን ሆኖ ውሏል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በቀን 01/05/2018 ዓ.ም 26,901 የተሽከርካሪ ፍሰት በማስተናገድ 820,230 ብር በመሰብሰብ ከፍተኛ ፍሰትና ገቢ የተገኘበትን ቀን ማስመዝገብ ችሏል፡፡
ከዕለት ወደ ዕለት የተሽከርካሪ የማስተናገድ አቅሙን እያሳደገ የመጣው የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ አገልግሎት በጀመረበት 2007 በጀት ዓመት በቀን በአማካኝ 12ሺ ተሽከርካሪዎችን በማስተናገድ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚገኘው የደንበኞች ፍላጎት በማርካት የማስተናገድ አቅሙን እያሳደገ የሚገኘው የፍጥነት መንገድ በአሁን ጊዜ በቀን ከ 22,000 ሺ በላይ ተሽርካሪዎችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡
ይህም የክፍያ መንገዱ ደህንነቱ የተጠበቀ ፣ ምቹና ዘመናዊ የክፍያ መንገድ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ማሳያ ነው፡፡