የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተፕራይዝ የተሸከርካሪ ክብደት መቆጣጣሪያ ቦታዎችን ከ3 ወደ 19 ማሳደጉን ገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተፕራይዝ የተሸከርካሪ ክብደት መቆጣጣሪያ ቦታዎችን ከ3 ወደ 19 ማሳደጉን ገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ – አዳማ የፍጥነት መንገድ ከጭነት ገደብ በላይ በጫኑ ተሸከርካሪዎች በሚያስከትሉት ጉዳት ምክንያት ከታሰበለት የጊዜ ገደብ ቀድሞ አገልግሎት መስጠት እንዳያቆም ከተፈቀደው ክብደት በላይ የጫኑ ተሸርካሪዎችን መቆጣጠሪያ ቦታዎች ቁጥር መጨመሩን አስታውቋል፡፡ በዚህም ቀድሞ ከነበሩት ሶስት የክብደት መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች በተጨማሪ በአስራ ዘጠኙም የመግቢያ በሮች ላይ የተገጠሙትን የክብደት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂዎችን በማስተካከል ተግባራዊ አድርጓል፡፡

 

የክብደት ቁጥጥሩ ባለፉት 2 ሳምንታት የተጀመረ ሲሆን በመንገዱ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ከመቀነሱ በተጨማሪ ፈጣን መንገዱ ያለ እድሜው እንዳይጎዳ እንዲሁም የአገልግሎት ደረጃውን ለማስጠበቅ ያግዛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለጥገና የሚወጣውን ወጪ ከመቀነሱም በላይ  በጥገና ወቅት በገቢው ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ይቀንሳል፡፡

የክብደት ቁጥጥሩ የሚደረገው በሲስተሙ በመታገዝ ሲሆን እንደ ተሽከርካሪው አይነት የሚለያይ ሆኖ በአጠቃላይ እንዲሁም በአግዝል ክብደት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ለምሳሌ ለመለስተኛ የጭነት ተሸከርካሪ ባከ 3 አግዝል 18 ቶን ፤ለገልባጭ ተሸከርካሪ 26 ቶን… ሲሆን ከ55 ቶን በላይ በልዩ ሁኔታ ካልተፈቀደ በስተቀር ፈጣን መንገዱን መጠቀም ክልክል ነው፡፤

በአሁኑ ወቅት ከተፈ ቀደው በላይ ትርፍ ጭነት የጫኑ ተሽከርካሪዎች ሲኖሩ ለጊዜው የግንዛቤ ማስያዝና አስተምሮ የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ፡፡ በቅርቡ ግን በጥናት የተደገፈ ቅጣት ተግባራዊ ይሆናል፡፡

አሽከርካሪዎች ይህን ተገንዝበው የሀገር ሀብትና የራሳቸው ንብረት የሆነውን ፈጣን መንገድ ለመጠበቅ ሀላፊነታቸውን አንዲወጡ ተጠቁሟል፡፡