የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ለበርካታ የአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል መፍጠሩ ተገለፀ ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ለበርካታ የአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል መፍጠሩ ተገለፀ ፡፡

በአዲስ አበባ – አዳማ የክፍያ መንገድ ክልል ዙሪያ የሚገኙ ከ347 በላይ የሚሆኑ የአካባቢ ማህበረሰብ የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

መንገዱ ከቱሉ ዲምቱ እስከ ወለንጪቲ ኬላ (መግቢያ) ድረስ 78 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን በመንገዱ ዙሪያ ለሚገኙ የህብረተሰቡ ክፍሎች በጥበቃ ፣በፅዳት ፣በካፍቴሪያ አገልግሎት እንዲሁም በአካባቢ ጥበቃ የስራ ዘርፍ በማመቻቸት የህብረታቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መቻሉ ተነግሯል፡፡

በጥበቃ አገልግሎት የተሰማሩ ሰራተኞችን በ21 ማህበራት በማደራጀት ለ7 ሴትና 222 ወንድ እና 23 ሴቶችን በፅዳት እንዲሁም በ5 ማህብራት 21 ሴቶችን በካፍቴሪያ አገልግሎት በተጨማሪም 74 ወጣቶችን በአካባቢ ጥበቃ ስራ ውስጥ ማሳተፍ ተችሏል፡፡

ይኽውም ኢንተፕራይዙ ከአካባቢው  ማህበረሰብ  ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር አስችሏል፤ ህብረተሰቡ መንገዱንና የተለያዩ ንብረቶችን በባለቤትነት ስሜት እንዲያዩ መልካም አድል ፈጥሯል፤ በኢንተፕራይዙና በህብረተሰቡ መካከል መተማመን ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እነዲኖር አስችሏል፡፡

በቀጣይ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት ለመስራት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡