የትራንስፖርት ሚኒስቴር የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሴት ሰራተኞች ዕውቅና ሰጠ፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሴት ሰራተኞች ዕውቅና ሰጠ፡፡

በትራንስፖርት ሚኒስቴር የሴቶች፣ ወጣቶችና ኤች አይ ቪ ኤድስ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት በስሩ ለሚገኙ ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አፈጻጸም ላገኙ ሴት ሰራተኞች ዕውቅና ለመስጠት ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በኦፕሬሽን ስራ ላይ የተሰማሩት ወ/ሪት ትዕግስት ለታ ከኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ ከሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዎስ የዕውቅና እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ኢንተርፕራይዙ ከትራንስፖርት ሚኒስቴር በወረደ አቅጣጫ መሰረት በትራንስፖርት ዘርፍ ውጤታማ ለሆኑ ሴት ሰራተኞች ዕውቅና ለመስጠት የሚከተሉትን አራት መስፈርቶች እንደግብዓትነት የተጠቀመ ሲሆን እነሱም፡-

  1. በ ውጤት ተኮር (BSC) ዕቅድ የተሻለ አፈጻጸም ያላት
  2. በስነ ምግባሯ የተመሰከረላት
  3. ሴቶችን ለመደገፍ ለማበረታታት ዝግጁ የሆነች እነዲሁም
  4. እንደተቋሙ ተጨባጭ ሁኔታ የስራ ብቃት ያላት የሚሉት ናቸው፡፡

ይኸውም ሴት ሰራተኞች የሚኖርባቸውን ማህበራዊ ጫና ተቋቁመው በተሰማሩበት ሙያ ውጤታማ መሆናቸውን ከማበረታታት ባለፈ ለሌሎች ሴቶች እንደአርዓያ በመሆን መነሳሳትና የይቻላል ስሜት በመፍጠር ለተሻለ ውጤት እንዲነሳሱ ማድረግ የፕሮግራሙ ግብ ነው፡፡