የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2010 ዓ.ም ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር 21% ጭማሪ ማሳየቱ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2010 ዓ.ም ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር 21% ጭማሪ ማሳየቱ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የሚያስተዳድረው የአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ በ 2010 ዓ.ም የዘጠኝ ወር ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር 21% ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በቀን በአማካይ ከ 19 ሺ በላይ ተሽከርካሪዎችን እያስተናገደ የሚገኘው የፍጥነት መንገድ ያልተቋረጠ የ24/7 የክፍያ መንገድ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህም በ2010 ዓ.ም በዘጠኝ ወር 5.225.191 ተሽከርካሪዎችን በማስተናገድ ከ 173 ሚሊየን በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

ይህ ገቢ ቀጥታ ከክፍያ መንገድ አገልግሎት የተገኘ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ከልዩ ልዩ ገቢ ማለትም ከማስታወቂያ ቦታ ኪራይ፣ ከመንገድ ሀብት ጉዳት ካሳ ክፍያ፣ ከተሸከርካሪ ማቆያና መጎተቻ… አገልግሎቶች ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡

በአጠቃላይ ከተለያዩ አገልግሎቶች ከ 182 ሚሊየን ብር በላይ ማስገኘት የቻለው የአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ በቀጣይም የአገልግሎት ደህንነትና ጥራትን በጠበቀ መልኩ የደንበኞችን ፍላጎት በማርካት ገቢውን ለማሳደግ እነደሚሰራ ተገልጿል፡፡