የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተፕራይዝ የ2010 በጀት አመት የዘጠኝ ወር ሪፖርት የስራ አፈፃፀም ምዘና አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተፕራይዝ የ2010 በጀት አመት የዘጠኝ ወር ሪፖርት የስራ አፈፃፀም ምዘና አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተፕራይዝ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ምዕራፍ በ2010 ዓ.ም እቅድ 10 ስትራቴጂካዊ ግቦች እንዲሁም 11 የማስፈጸሚያ ፕሮግራሞችን ነድፎ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

በዘጠኝ ወራትም 5,821,235 የትራፊክ ፍሰት በማስተናገድ ከክፍያ መንገድ አገልግሎት ብር 173,732,732.00 መሰብሰብ የቻለ ሲሆን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር 21% ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ገቢን ከማሳደግ ባሻገር የመንገዱን ደህንነትና ምቾት ለማረጋገጥ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም አገልግሎት አየሰጠ የሚገኘው የአዲስ አበባ -አዳማ የፍጥነት መንገድ የክፍያ መሰብሰቢያ እና የክብደት ቁጥጥር ስርዓት ላይ ማሻሻያ በማድረግ ይገኛል፡፡

ኢንተርፕራይዙ በያዝነው አመት 229 የሚሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብን በ21 ማህበራት በማደራጀት የፈጣን መንገዱን ጥበቃ የስራ እድል በመፍጠር

እንዲሁም 150ሺ ብር ወጪ በማድረግ ለአካባቢው ማህበረሰብ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ በማካሄድ ማህበራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

ከዚሀም በተጨማሪ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ እንቅስቃሴ ረገድ አለም አቀፍ የፋይናንስ አመዘጋገብ ስርአት ትግበራ (IFRS) ፤ የችግኝ ማፍያ ጣቢያ ፤ እንዲሁም የመንገድ ላይ መብራት ማስፋፋት ፕሮጀክቶች የሚጠቀሱ ስራዎች ናቸው፡፡

በ9 ወራት ከተከናወኑ ስራዎችን በትኩረት የገመገመው ተቋሙ የተገልጋይ እርካታ አለመለካቱ የለውጥ ስርዓት ግንባታ በሚፈለገው ደረጃ አለመሳካቱ እንዲሁም የሰራተኞች አፈፃም በውጤት ተኮር ስርዓት መለካት አለመጀመሩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸው አስቀምጧል፡፡

 

አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሶስት አመት ከስምንት ወር በላይ ያስቆጠረው የአዲስ አበባ -አዳማ የፍጥነት መንገድ ያልተቋረጠ የ24/7 የክፍያ መንገድ አገልግሎት መስጠት መቻሉ ከአካባቢ ህብረተሰብ ጋር መልካም ግንኙነት መመስረቱ እነዲሁም ወቅታዊ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ የትራፊክ ፍሰትና የገንዘብ ገቢ እንዲጨምር ማድረጉ የተነሱ ጠንካራ ጎኖች ሲሆኑ የትራፊክ አደጋን በተፈለገው ደረጃ መቀነስ አለመቻሉ እንደድክመት ተነስቷል፡፡

በቀጣይም የታዩ ደካማ ጎኖችን በጥልቀት በማየትና ማስተካከያ በማድረግ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ከዚህ በተሻለ መልኩ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ የኢንተፕራይዙን ራዕይ ከግብ ማድረስ እንደሚገባ አቅጣጫ  በመውሰድ ግምገማው ተጠናቋል፡፡