የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የክፍያ መንገዱን ደህንነትና ምቾት ማሳደግ ለኢንተርፕራይዙ ገቢ መጨመር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የክፍያ መንገዱን ደህንነትና ምቾት ማሳደግ ለኢንተርፕራይዙ ገቢ መጨመር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ምቹና ዘመናዊ አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ አገልግሎቱን በላቀ መልኩ ለማስኬድ ያስችል ዘንድ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በዚህም የአገልግሎት ጊዚያቸውን የጨረሱ የመንገዱ ንብረቶችና የተጎዱ የአስፓልት መንገዶችን በመለየት አስቸኳይ ጥገና ማድረግ፤ የቅድመ አደጋ መከላከል እንዲሁም በአደጋ ጊዜና በድህረ አደጋ ወቅት መደረግ ስለሚገባ ጥንቃቄ ግንዛቤ ማስያዝ እና መንገዱን ፅዱና ውብ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

በተጨማሪም ላለፉት ሶስት ዓመታት የተገኙ ተሞክሮዎችን በመቀመር የ24/7 ያልተቌረጠ የመንገድ ላይ ቅኝት በማድረግ ከመንገድ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላትና ለትራፊክ አደጋ መንስኤ የሚሆኑ እግረኛ፣ እንስሳት፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪቸዎች ወደ መንገዱ ክልል እንዳይገቡ የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢንተርፕራይዙ የመንገድ እና የትራፈክ ደህንነት አስተዳደር ቡድን ገልጸል፡፡

በአዲስ- አዳማ የፍጥነት መንገድ የተጠቃሚዎች ቁጥር ከእለት ወደ እለት እያደገ እንደመሆኑ መጠን የመንገዱን ደህንነትና ምቾት በማስጠበቅ ገቢ እነዲጨምር ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም በቀጣይም ኢንተርፕራይዙ የመንገድ ደህንነትን ለማስጠበቅ  ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡