በፍጥነት መንገዱ ላይ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

በፍጥነት መንገዱ ላይ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

ትኩረቱን የመንገድ ደህንነት ላይ ያደረገው ውይይት ማክሰኞ ግንቦት 7/2010 ዓ.ም በሞናርክ ሆቴል ተካሂዶ ውሏል፡፡ በውይይቱ የኢንተርፕራይዙ የበላይ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል፤ የሚጠፋውን የሰው ህይወት ለመታደግና የሚወድመውን ንብረት ለመጠበቅ መደረግ ስለሚገቡ ነገሮች እንደመነሻ የተነሱ ሲሆን  በተለይም ውይይቱ በአዲስ-አበባ አዳማ የክፍያ መንገድ ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ የትኩረት አቅጣጫው ነበር፡፡

በቀን ከሃያ አንድ ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን በማስተናገድ አቅሙን እያሳደገ የመጣውን የፍጥነት መንገድ ከአደጋ የተጠበቀ በማድረግ የመንገድ ደህንነትን በስፋት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡

ኢንተርፕራዙ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ወጥ የሆነ አሰራር አለው; ከግንዛቤ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የተሰሩ ስራዎች እነዴት ይታያሉ; ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በቅንጅት የመስራት ሁኔታው እነዴት ይገመገማል; የሚሉና በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር በዕለቱ ከተሸከርካሪ ማረጋገጫ ፈቃድ አሰጣጥ ጀምሮ በሚወጡ የትራፊክ ህግና ደንቦች እንዲሁም አተገባበርና ቁጥጥር ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በመጨረሻም የኢንተርፕራይዙ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ ከድር ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የተሰጡ አስተያየቶች ገንቢ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ እነዲሁም በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት፣ ከአካባቢው ህብረተሰብ፣ ከአሽከርካሪዎች እነዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር በቅንጅት መስራት እነደሚገባና ይህን እንቅስቃሴ ቀጣይነት እነዲኖረው በማድረግ ወደ ተግባር ማውረድ እነደሚያስፈልግ በማንሳት ውይይቱን አጠቃለዋል፡፡