አዲሱ ብሔራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲ!

አዲሱ ብሔራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲ!

አዲስ የተዘጋጀው ብሔራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲ መሰረት የክልል መንግስታት በአስተዳደር ወሰናቸው ሥር የአስፓልት መንገዶችን እንዲገነቡ ያስቻለ ነው ሲሉ የትራንስፖርት ሚኒስቴሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከኤፍ ቢ ሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡

 

በክልሎች የሚገነቡ የአስፓልት መንገዶች ወጪያቸው በክልሉና በፌደራል መንግስት ይሸፈናል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም እንደ ሀገር ከ300 ኪ.ሜ የማይበልጠውን የፍጥነት መንገድ ወደ #2ሺ ኪ.ሜ ለማሳደግ እቅድ መቀመጡን ሚኒስተሯ ገልፀዋል፡፡high flow

 

ቀጠናዊ ትስስርን አንዱ ዓላማው ባደረገው በዚህ ፓሊሲ መሰረት አሁን ላይ ሀገራችንን ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኙ ከ6 ያልበለጡ መንገዶችን በ14 በማሳደግ ከ20 በላይ መንገዶች እንዲኖሩ በዕቅድ መያዙንም ገልጸዋል፡፡

 

ብሔራዊ የትራንስፓርት ፖሊሲው በትራንስፖርት ዘርፉ በከተማና በሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገለግሎት የውጪ ባለሀብቶች ከሀገር ወስጥ ባለሀብቶች ጋር በመጣመር ከ49 በመቶ ባልበለጠ ድርሻ እንዲሳተፉ የሚፈቅድም ነው ብለዋል፡፡