የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አመራሮች እና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ድጋፍ አደረጉ ።

በተደረገው አጠቃላይ የሰራተኞች ስብሰባ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ደጀን በመሆን በሁሉም አቅጣጫ የሀገርን ሠላም ለማስከበር ለሚከፍለው መስዋትነት በተሰማሩበት የሙያ መስክ ከማገልገል ባሻገር የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት  ቃል ገብተዋል ።

ለሀገር ጥሪ የሚሰጥ ምላሽ ከዚህም በላይ ሊሆን ይገባል ያሉት የኢንተርፕራይዙ ዋና ስራ አስኪያጅ  አቶ ሙስጠፋ አባሲመል ሰራተኛው ላሳየው የሀገር ፍቅር ስሜት ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የኢንተርፕራይዙ ሰራተኞችም በደመወዝ ከመደገፍ ባለፈ በየትኛውም ሁኔታ ዉስጥ ለሚደረግ የሀገር ጥሪ ዝግጁ ነን ሲሉያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል ።